, 16 tweets, 3 min read
ምን ያህሎቻችሁ ናችሁ የደም እጥረት በ ኢትዮጵያ ኢንተር ሃኪሞች መካከል የውዝግብ መንስኤ መሆኑን የምታውቁት?

ይህ ትሬድ ጎንደር፣ ጅማ እና ሃዋሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች ውስጥ የሚገኙ ኢንተር ሃኪሞችን በቃል በመጠየቅ የተዘጋጀ ነው።

አንብቡት ✌
በነዚህ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች ደም ለሚያስፈልጋቸው ህመምተኞች ትራንስፊውዝ ማድረግ የኢንተርን ሃኪሞች ሃላፊነት ነው።
የህመምተኛውን የደም አይነት ከመለየት ጀምሮ ደም ባንክ ሄዶ ደም መጠየቅ፥ የተጠየቀው የደም አይነት ወድያውኑ ስለማይገኝ ወረፋ መያዝና እየተመላለሱ ደም መምጣቱን መጠየቅ፥ በለስ ከቀናም ክሮስ ማች አሰርቶ ደሙን ለህመምተኛ መስጠት ያካትታል።
የምግባባቸውን 16 ኢንተር ሃኪሞች (ከሶስቱም ሆስፒታሎች ማለቴ ነው) እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቄያቸዋለሁ👇

ሀ/ የደም ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ደም እንደሚያገኙ

ለ/ በብዛት የሚያገኙት የደም አይነት እና የማያገኙት የደም አይነት
ሐ/ በአማካኝ ደሙ ከተሰበበ ምን ያህል ጊዜ የቆየ ደም እንደሚያገኙ

መ/ ከሆል ብለድ ውጪ የተለያዩ የደም ሴሎችን የያዙ የደም ፖኬጆችን በቀላሉ ያገኙ እንደሆነ

ሠ/ ህፃናትን ደም ትራንስፊውዝ ሲያደርጉ የሚባክህን ደም አለ ወይ
ረ/ ደም በጊዜው ባለማግኘታችሁ ምን አጋጥሟችሁ እንደደሚያውቃል

ለነዚህ ጥያቄዎች የሰጡኝን ምላሽ ጠቅለል አድርጌ እንደሚከተለሁ አቀርባለሁ
👉አብዛኞቹ ሃኪሞች እንደሚስማሙት የደም ጥያቄ እንዳቀረቡ ወዲያውኑ ምላሽ እንደማያገኙ ነው። የአቅርቦት ችግር በብዛት የሌለባቸው እንደ የደም አይነት A እና AB እራሱ ጥያቄ ከቀረበ ከሰዓታት በኃላ ነው ለታካሚዎች የሚደርሱት።
👉 A+/- እንዲሁም AB የደም አይነቶች በብዛት ይገኛሉ። O- ደግሞ ከብዙ ድካም በኃላ የሚገኝ የደም አይነት ነው።
👉 ፍሬሽ ደም ማግኘት እንደቅንጦት የሚታይ ጥያቄ መሆኑን ሃኪሞቹ በአንድነት ይስማሙበታል። ለየብቻ የተዘጋጁ የደም ሴሎች የደም ባንኩ በብዛት ስለማያቀርብ (እንደሰማነው ይህ ፖኬጅ አ/አ ብቻ ነው የሚገኘው) .......
....ሃኪሞች ከተሰበሰበ ብዙ ጊዜ ያልቆየ ደም ምርጫቸው ያደርጋሉ በተለይ የፕላትሌት የደም ሴል ቁጥራቸው እጅጉኑ አንሶ ለሚገኙ ህሙማን። ነገርግን ፍሬሽ ደም ለማግኘት ረዘም ያለ ጊዜ እና የደም ማዕከሉ ጋር የተለየ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል።
👉 የደም እጥረት ባለበት ሃገር ውስጥ ደም አባካኝ እንደመሆን ሃጢያት የለም። ኢትዮጵያ ለህፃናት የተዘጋጀ አነስተኛ መጠን ያለው የደም ከረጢት የላትም ስለዚህ አንድ ህፃንን ትራንስፊውዝ ለማድረግ ለአዋቂዎች የምንጠቀመውን ዩኒት እንጠቀማለን...
... ህፃናት ደግሞ በኪሎዋቸው መጠን ደም ስለሚወስዱ የአዋቂዎችን ሙሉ ከረጢት ደም አይጨርሱም ስለዚህ ልባችን እያዘነ ወርቅ የሆነውን ደም እንጥላለን 😧
👉 ደም እንቁ ነው! በቀላሉ እንደተፈለገ አይገኝም።

እንቁም ስለሆነ ብዙ ኦፕሮሽኖች በየቀኑ ይሰረዛሉ። በሃኪሞች መሃከልም የውዝግብ መንስኤ ይሆናል! አንተ ስንት ቀን ጠብቀህ ያገኘዉን ደም ፥ ደም የሚፈሳት እናት ካለች ለሷ ደሙን መልቀቅ ስላለብህ።
ሲልም ለደም ብቻ ብለው ህመምተኞች ከየሆስፒታሉ ወደ ሪፈራል እና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች ሪፈር ሲደረጉ እና ሲጉላሉ ማየት በጣም ያስከፋል።
በመጨረሻም ሊታወቁ የሚገቡ እውነታዎች:

- ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ሰፊ የሆነ የደም እጥረት አለ።

- ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ብዙ ደም የሚያስፈልጋቸው ህሙማን አሉ።
- @EthiopianBlood ለሁል ጊዜ ቀናነታችሁ እናመሰግናለን። ለህፃናት አዳዲስ ፓኬጆችን አዘጋጁልን። እንደሁልጊዜው በአዳዲስ ነገር አስደምሙን።

መልካም የደም መለገስ ቀን!
Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh.

Enjoying this thread?

Keep Current with Firew Asrat

Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

Twitter may remove this content at anytime, convert it as a PDF, save and print for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video

1) Follow Thread Reader App on Twitter so you can easily mention us!

2) Go to a Twitter thread (series of Tweets by the same owner) and mention us with a keyword "unroll" @threadreaderapp unroll

You can practice here first or read more on our help page!

Follow Us on Twitter!

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just three indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3.00/month or $30.00/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!