[1] 😍 የዘሩባቤል "ኢትዮጵያ" የተሰኘ ሙዚቃው ማጠንጠኛ "የኢትዮጵያ አምለክ ስራ" ላይ ነው። ህዝቧ ተስፋው የተሟጠጠ፣ እምነቱ የተናጋ፣ ስሪቱ የተምታታ ሲመስል "የኢትዮጵያ አምላክ" ከመንበሩ በአርምሞ እንደማይመለከት በእነኚህ ስንኞች እንዲህ ይላል
[2]
“ከፈተው ጠራ ሰማይ ሲያስውብሽ ሁሉም እንዲያይ
ከፈተው ጠራ ሰማይ እሱ እንዳለው ሲሆን አለም እንዲያይ”
[3] 😍 “ኢትዮጵያዊነት ላይ ፤ ሀገር መውደድ ላይ ፤ አንድነት ላይ” የሚየተኩረው የጃኖ ባንዶቹ "ሀገሬን እወዳለሁ" አሁን ካለንበት ሀገራዊ ምስቅልቅል ስሜት የሚያሳርፍ ጭው ባለ በረሀ አንደተገኘ የትንሽ ግራር ጥላ ነው።
[3] ... ምንም እንኳን አባይ በአንድ ቢያስተሳስረንም መድህን የሚሻ ያልጠገገ ቁስል አለን። ጊዜ እየጠበቀ የሚያመረቅዝ። ሰላምና አንድነታችንን የሚያውክ። ከዚህ አንፃር ሲታይ የጃኖዎች የጥበብ ስራ ዋጋው ትልቅ ነው።
ጥራኝ የሀገሬ ሰው
እምባዬን ደባብሰው
ሰው መሆን አማረኝ
ውርደት አማማረኝ
እኔ እኖራለሁ በሀገሬ (x2)
እኔ እወዳለሁ ሀገሬን (x2)
[4] 😍 ስለ ቴዲ አፍሮ ስራ ምን ሊባል ይችላል?! አንድያውን በልባችን ስለ ጥበብ ነግሷል። ሲቃችንን ቃትቶ ለመንፈሳችን ብርታት ለአንደበታች ውብ ቃላትን አቀበለን። "ደግሞ ለአባይ" አለና እኛን ሁሉ ወክሎ ለምትደነፋብን ግብፅ መለሰላት።
[4] ... ድርድሩ ይቅደም ብለን ውጠን ያስቀረነው እንደ እቶን የሚፋጀው ሽለላችንን "ቼ በለው" እያለ ነገረልን። ይህ የቴዎድሮስ ሙዚቃ አባይ ላይ ለሚደረግ ድርድር ሁሉ አጃቢ ሙዚቃችን ይሆናል። ለአሁኑም ለወደፊቱም !!
ቼ በለው!
የተቆጣ እንድው
ቼ በለው!
ፍቅር ታግሶ
ቼ በለው!
የሚባላ እሳት
ቼ በለው!
ይሆናል ብሶ!!!
ማን ዝም ይላል ደሞ ዜጋ
ደሞ በአባይ!
ሳንጃው ፀብ አይመርጥም
ለቁረጠው አለ እንጂ
የራሴን ውሃ ጥም
[5] እነኚህን ከላይ የጠቀስናቸውን ሶስት ሙዚቃዎች ለየብቻቸው የተለያዩ ግን ደግሞ በእኩል የምንፈልጋቸውን እና ማለት የምንወደውን እውነቶች ይገልጣሉ። አብረው ተሰናስለው ሲሰሟቸው የሚሰጡት ስሜት ግን ልዩ ነው።
[6] እምነት፣አንድነት እና ጀግንነት በተራክቦ የፈጠሩት ልዩ አለም ውስጥ ይከታሉ። ሙዚቃዎቹ በህብረት የመጣንበትን የታርክ ትውስታ ያስቃኙናል፤ መጠጊያ በምንላት ሀገር ኢትዮጵያ እምነት እንዲኖረን ያፅናኑናል።
[7] ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ብቸኛ አማራጫችን እንደሆነም ያሳያሉ። ደግሞም እንዲህ ነው ሚያምርብን 💚💛❤️
Share this Scrolly Tale with your friends.
A Scrolly Tale is a new way to read Twitter threads with a more visually immersive experience.
Discover more beautiful Scrolly Tales like this.
