ህብረ ትርኢት Profile picture
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
Oct 18, 2020 17 tweets 3 min read
እንደምን ውላችኋል ቤተሰብ? ሁሉ ሰላም? ሁሉ ተማም?
እስኪ እባካችሁ አማክሩን ❣️

A Thread
ጊዜ ወስዳቹ አንድታነቡት ከአክብሮት ጋር እንጠይቃለን ትላንት የቅዳሜ የሙዚቃ ምርጫ ፕሮግራማችንን ሳንሰራ ስለቀረን በጣም ከፍቶን ነበር። ወዳጆቻችን ተደስተው በናፍቆት እንደሚጠብቁን ሁሉ አልፎ አልፎ ከቅጂ መብት (copy right) ጋር በተገናኘ “ይሄ ነገር ልክ ስራ ነው?” የሚሉም አስተያየቶች ይደርሱናል።
Oct 17, 2020 9 tweets 3 min read
አበሩስ እንዴት አደራችሁ😍

ከሰሞኑ የተለቀቀውን የ ጠረፍ/Terry Teref ሙዚቃ ስራ ስሙትማ 💖

Terry የምትታወቀው በአንጋፋ ድምፃውያን የተሰሩ የሚጣፍጡ የድሮ የፍቅር ዘፈኖችን በራሷ ዘይቤ በመስራት ነው።

መልካም ቅዳሜ ለሁላችሁም
A thread .... ሀገሬ ኢትዮጵያ ለምለሟ አበባዬ
ሳስብሽ ይፈሳል እምባዬ በላዬ
ሰላም ላንቺ ይሁን ለውዲቷ እናቴ
ካለሁበት ቦታ ከልብ ከናፍቆቴ
ይሄም ሀገር ሀገር ሀገር ይላል ሀገር ይሄ ሀገረ ብርቁ
አህም እኔም ሀገር ሀገር አለኝ ሀገር የሚታይ በሩቁ
(የአስቴር አወቀ)
Oct 15, 2020 18 tweets 4 min read
ሐሙስ የቀን ቅዱስ
💚🧡❤️
ሳምንታዊ የአይሬ ፕሮግራማችንን ይዘን ቀርበናል
💚🧡❤️

ገባ ገባ በሉ ቦታ ቦታችሁን ያዙልን
🙏

#ReadMeryArmde

🥁🎹🎸🎺🎷🎹🎼🎶🎚️ በክራር ጨዋታዋ እና በወፍራም ድምጿ በማንጎራጎር የምትታወቀው አንጋፋዋ አርቲስት ሜሪ አርምዴ የዛሬው የአይሬ ዝግጅታችን ትኩረት ናት።

በ1915 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ዶሮ ማነቂያ ከሚባለው ሰፈር ነው የተወለደችው።
Sep 27, 2020 7 tweets 2 min read
ወዳጆች ይህንን የጥላሁን ገሠሠ "አምሳሉ" የተሰኘ ሙዚቃ ስራ ታውቁ ኖርዋል?

አንዲት ወዳጃችን ስሜ ይቆይ ብላ ይህንን ድንቅ ሙዚቃ አቀብላናለች። እግዜር ይክብርልን ብለናል።

ለኛም ይሄ የመጨረሻው ሙዚቃችን ይሆናል ለዛሬ

ግጥሙን ልብ በሉ 💚💛❤️ አበባው ለምለሙ ዛፉ ሳሩ ቅጠሉ
በፍጥረት አለም ላይ አምሮ የሚታይ ሁሉ
ውብ የሆነው ነገር የሚያምረው በሙሉ
ሀሩ ቀጭን ኩታው ለጌጥ እንቁና ሉሉ

Sep 27, 2020 6 tweets 1 min read
"በባይተዋር ጎጆ" ደግሞ ከጥላሁን ገሠሠ በጣም ከሚደነቅለት የፍቅር ዘፈኖቹ ውስጥ ደግሞ።

እያንዳንዱ ስንኝ ያዘለው ተማፅኖ ናፍቆት ስስት እና ፍቅር አጃይብ ያስብላል ❣️❣️❣️ በባይተዋር ጎጆ በባይተዋር አልጋ
እንግዲህ ለሊቱ ዋ እንዴት ይንጋ

Sep 27, 2020 6 tweets 1 min read
መልካም ልደት ለሙዚቃው ንጉስ ጥላሁን ገሠሠ ❤️
ድንቅ ስራዎቹን ትቶልን አልፉዋል ፤ እግዚያብሔር ነፍሱን በገነት ያኑራት እያልን ፤ "የዘንባባ ማር ነሽ" የተሰኘውን ሙዚቃውን እንጋብዛቹ 😍 የዘንበበ ማር ነሽ እም ወለላሽ የረጋ
አልደርስብሽ አልኩኝ አሀ እጄን ብዘረጋ
የዘንባባ ማር ነው ፍቅርሽ
ቄጤማን ይመስላል ጸጉርሽ
ምርኩዜ ወደቀ በትሬ
አይን አይንሽን ሳይ ተገትሬ

Sep 27, 2020 5 tweets 2 min read
ውድ ቤተሰቦቻችን መስቀል እንዴት እያለፈ ነው?

ዛሬ ወዲህ ክርስትያን ቤተሰቦቻችን መስቀል በዓልን የሚያከብሩበት ወዲህ ደግሞ የሙዚቃ ንጉሳችን ጥላሁን ገሰሰ የልደት ቀኑ የሚታሰብበት ድርብ በዓል ነው። ለንጉሳችን ካለበት ከገነት አጸድ የእንኳን ተወለድክ መልዕክታችን እንዲደርሰው ከተጫወታቸው ሙዚቃዎች ጥቂቶችን እየሰማን እናስበዋለን። የመጀመሪያችን የምናደርገው "የጠላሽ ይጠላ"ን ነው።

ፍቅሬ ሆይ ልንገርሽ ምንም ይሁን ምንም
እዚህ ቦታ ቀራት ቢሉኝ እኔ አላምንም
Sep 26, 2020 20 tweets 6 min read
የገነንዳ ሰብ እንኳን አሰናሁም 😍

ዛሬ የቅዳሜ ምርጫ ፕሮግራማችን ላይ የመስቀል ዋዜማ እናከብርበታለን

ሙዚቃ ምርጫዎቻችሁንም በፍቅር እናስተናግዳለን ❤️ ክብር የሚገባቸውን የጉራጌ ባሪቅ (አዛውንቶች) ይህንን ባህል ስላቆዩልን እያመሰገንን እንጀምር
መሐመድ አወል "የጆካ ባሪቅ" እያለ የጉራጌ አዛውንቶች ይመርቃል

መልካም የመስቀል በዓል ይሁንላቹ
Sep 23, 2020 5 tweets 1 min read
ሰላም ቤተሰቦች

እፍፍፍ ክንፍ ቅብጥብጥ የሚያደርግ ፍቅር ይዟችሁ ያውቃል የለ?! ጣምናው ቢለያይም በፍቅር ፍንክንክ፣ ፍልቅልቅ ባለ ደስታ ስምጥ ብሎ ያላለፈ መቼም አይርም ብለን እንገምታለን። ካለም፥ ምርቃታችን ዝንጥንጥ ቅብጥብጥ የሚያደርግ ፍቅር ይስጥህ ይስጥሽ ነው (አሜን በሉ)

ከምንም በላይ ግን፤ የሚወዱት ሰው በሚወዱት መጠን ወይም ከዛ በላይ ይወዳኛል ብሎ ማመን መታደል ነው እንላለን።

በዚህ ምሽት የምንጋብዛችሁ የአስቴር አወቀ “ፍቅር ፍቅር” የሚለውን ሙዚቃ ነው።
Sep 22, 2020 5 tweets 1 min read
ስሙማ 😍 ልክ ወደ 11 (ከረፈደ 12) ስዓት አካባቢ ለባብሰን ከቤት የምንወጣውስ 😅 'ዎክ እናድርግ' እንልና ጥንድ ለጥንድ ሆነን ሰፈሩን ትላንት እንዳልዞርነው ዛሬም በአዲስ ጉልበት በተለመደው መስመር የባጥ የቆጡን እያወራን መሽቶ እስክንለያይ መዞር 😍 ሃና ግርማ "ጨረቃ" የተሰኘው ስራዋ ላይ ጉዳችንን ዝርዝር አድርጋ አስፍራዋለች 😅
Sep 22, 2020 9 tweets 2 min read
አበሩስ በምነን 😍 ሰላም ነው? ምሳ ተበላ? ተፍ ተፍ እያልን ነው?

የዘሪቱ ከበደ “የኔም አይን አይቷል” ጋብዘናል

ወደ ማታ ደሞ ከች እንላለን፤ ኑሮ እና ብልሃቱ ካሯሯጠን በኋላ 😅 አንዱን ሊያድነው
አንዱን ሊያሞኘው
ካንዱ በፈሰሰው
አንዱን ሊያርሰው
ላዘነው ሰው ምነው
ቢያካፍለው ቢያቻችለው
ለተረፈው ምነው
በቃህ ቢለው
ይብቃህ ቢለው

Sep 21, 2020 6 tweets 2 min read
እንዴት አመሻችሁ ቤተሰቦች

ብሩህ ይሆናል!

በግልም እንደሀገርም ፈታኝ የሆኑ ነገሮች ገጥመውን ያውቃሉ። አቅል እስኪያስቱን የሚደርሱ መከራዎች አልፈውብናል። አልፈናቸው ግን እዚህ ደርሰናል። ይሄን ቀን ማየታችን ለዚህ ምስክር ነው። የዛሬውንም እናልፈዋለን። ነገ አዲስ ቀን ይወጣል። የጨለመው ይበራል። ክርምቱ አልፎ ጸደይ ይሆናል። እኔ አንተ አንቺ እኛ ባንድነት ሆነን ወደ ብሩህ ነገ እሻገራለን።

ጨልሞ አይቀርም አዲስ ቀን ይመጣል
ጸሀይ ትወጣለች ብርሀን ይሆናል
Sep 19, 2020 32 tweets 8 min read
ሰላም ሰላም የጮቤ ቤተሰቦች!

ዛሬ ቅዳሜ ነው 🎹🥁🎸🎷🎼
በቅዳሜ የዘፈን ምርጫ ፕሮግራማችን መጥተናል።
ቆንጆ ቆንጆ ሙዚቃዎች ተዘጋጅተዋል። የእናንተን የሙዚቃ ግብዣዎች ለመቀበል DMችን ክፍት ነው። ሹክ በሉን። አብረን እንገባበዛለን! ሰዎች አሉ በህይወታችን ውስጥ። ለመንገዳችን ብርሃን ይሆኑ። ፈገግታቸው ንጋታችንን እንደ ጠዋት ጮራ የሚያበስር። አዘቦቱ ስሜታችንን በረቂቅ ጥበባቸው አውዳመት የሚያደርጉ። ቀናችን አንድ ተብሎ የሚጀመርባቸው።
Sep 18, 2020 5 tweets 1 min read
መልካም ጁማ 🙏
ቤተሰብ

🙏💚💛❤

ገባኝ አሁን ገና ገባኝ አሁን ገና!

ከሰው ጋር ለመኖር አቋራጭ ጎዳና

ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና!!

አንድን መፃፍ ውስጡን አይተው ሳያጠኑ
ቢፈርዱበት ያሳዝነሰል በሽፋኑ

ለማስመሰል አልችል ብዬ ስላቃተኝ። ሌላ አይደለም የኔ ጠላት እራሴው ነኝ።
ከሰው ጋር አብሬ ለመኖር ለጊዜው ማስመሰል ባልችልም
እራሴን እስከማውቀው ድረስ ያን ያህል ክፉም አይደለውም

ግልፅነት ራሴን መሆኔ ቢለየኝ ሀዘኔ ያበቃል
ብከፋም በሰው ቂም አልይዝም
የልቤን ፈጣሪ ያውቃል
Sep 17, 2020 26 tweets 6 min read
ሐሙስ የቀን ቅዱስ
💚💛❤

ሳምንታዊ የአይሬ ፕሮግራማችንን ይዘን ቀርበናል❤

ገባ ገባ ቦታ ቦታችሁን ያዙልን🙏
#ReadZinetMuhaba
🎹🥁🎼🎧🎤🎷🎺🎻🎸 ቤተሰቦች ዛሬ በሳምንተዊው አይሬ መሰናዶአችን ስለ አንጋፋዋ እና ተወዳጇ ዚነት ሙሃባ ጥቂት ልናካፍላችሁ ወደናል።
Sep 17, 2020 11 tweets 2 min read
አበሩስ የተንቢ ሰላም አደራቹ 🤗

ዛሬ በንዋይ ደበበ "ድሃ ናት" የተሰኘውን ድንቅ ስራ ቀኑ ቢጀመር ምን ይለዋል😅

ይሄንን ለምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ ፤ እንዲሁም የሀገር እና የቤተሰብ ዋልታ ለሆኑት ደጋግ እናቶቻችን ይሁንልን 💚💛❤️ ጥሮ አዳሪ ለፍቶ አዳሪ
የእግዜር ድሀ ደክሞ ኑዋሪ
ደግ እሩህሩህ ልበ ቀና
በሰው ኑሮ የማትቀና
እንደልፋትዋስ ማን በለጣት
እድልዋ ነው የሚያጠቃት
ተዋት እሷን ተዋት
ተዋት ለኔው ተዋት ምስኪን ድሀ ናት

Sep 14, 2020 7 tweets 1 min read
አበሩስ ሰላም ነው 😍
ሰኞ መቼም ሰኞ ነው በተለይ ከበዓል ማግስት😅 እንግዲህ ቻል ማድረግ ነው። ይሄን ጣፋጭ ሙዚቃ እንጋብዝ 🙏

ተአምር ግዛው ፤ የጥላሁን ገሰሰን "በባይታዋር ጎጆ" እንዲህ አሳምራ ሰርታዋለች (ጥበቡን ያብዛልሽ ብለናል) በባይተዋር ጎጆ በባይተዋር አልጋ
እንግዲህ ለሊቱ ዋ እንዴት ይንጋ
ያረፈብህ ክንዴ አሀ ያለበስኩህ ኩታ
ያደርንበት ጎጆ አሀ ያሞቀን መኝታ
ሀቄን ይግለፅልህ አሀ የፍቅራን ሁኔታ

Sep 13, 2020 4 tweets 1 min read
እንዴት አመሻቹ ወዳጆች 😍
በዓል እንዴት አለፈ? መልካሙን ሁሉ እየተመኘን
የታደለ ሮባ "ከፍጥረት የግልሽ" እንጋብዝ

ከፍጥረት የግልሽ ያንቺ እንደተባለ
ገላዬ ከሌላ አልላመድ አለ አሀሀ
ተግባብቶ ለማደር የማይመች ሆኗል
ተፈቅሮ ለማፍቀር አሀሀ አሀዱ ብል አዲስ ህይወት
ተስኖኛል ምላሽ መስጠት
ምንም ሳይኖር ያጣሁባት
አልቻልኩም እንዳንቺ እኔ ልሆንላት
ዛሬም ሚስጥር ሆኖ አለ ይሄ ምክኒያት
Sep 12, 2020 4 tweets 1 min read
አመት በዓል ሲነሳ ምግቡ፣ መጠጡ፣ ቡናው፣ ጨዋታው ምኑ ልዩ ድምቀት ይሰጣሉ። ለድምቀቱ ሁሉ የበላይ የሚሆኑት ታዲያ በሸማ ያጌጡ ሴቶች ናቸው። ከድካማቸው ጥቂት አረፍ ብለው አቅም የፈቀደውን ቀሚሳቸውን ለብሰው ሲወጡ በዓሉ እንደገና አንድ ብሎ የሚጀምር እስኪመስል የተለየ ድባብ ይፈጥራሉ። ውበት፣ ክብር እና ሞገስ ባንድነት ባንዲት ሴት ላይ ይገለጣሉ። ሙዚቀኛው

ያምራል ጥለትሽ እቴ ያምራል ጥለትሽ
ያምራል ጥለትሽ ያ የመቀነትሽ

እንዳለው የበዓል ስራ ያደቀቀው ወገቧን ሸብ ያደረገችበት
Sep 11, 2020 5 tweets 1 min read
🌻መልካም አዲስ አመት ወዳጆች 🌻
ከሀገር ውጭ ለምንኖር ዛሬ መቼም የሀገር እና ቤተሰብ ናፍቆት ከባድ ነው
💚💛❤️ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ሰላም እና ፍቅር እንመኛለን 💚💛❤️

አስቴር አወቀ "ሀገሬ" ሀገሬ ኑሪ ሀገሬ ኑሪ
ሆኜ አልቀርምና እኔ እንደወፍ በራሪ
እመጣለሁና ዘንድሮ ለገና
መቼም ሰው ከሀገሩ ወጥቶ አይቀርምና
ዎይ ዎይ ዎይ

Sep 10, 2020 32 tweets 8 min read
ሐሙስ የቀን ቅዱስ
💚💛❤

ሳምንታዊ የአይሬ ፕሮግራማችንን ይዘን ቀርበናል❤

ገባ ገባ ቦታ ቦታችሁን ያዙልን ቤተሰብ🙏 ዛሬ የምናጠናቀቅው አመት በግልም እንደ ሀገርም ስኬቶችን ያስመዘገብንበት በዛው ልክ አስጨናቂ ጊዜያትን ያሳለፍንበት አመት ነበር። አይታለፉ የሚመስሉትን አልፈን አይደርሱበትም የተባለው ላይ ደርሰን አመቱ እነሆ አለቀ!