ሐሙስ የቀን ቅዱስ
💚💛❤
ሳምንታዊ የአይሬ ፕሮግራማችንን ይዘን ቀርበናል❤
ገባ ገባ ቦታ ቦታችሁን ያዙልን🙏
#ReadZinetMuhaba
🎹🥁🎼🎧🎤🎷🎺🎻🎸
ቤተሰቦች ዛሬ በሳምንተዊው አይሬ መሰናዶአችን ስለ አንጋፋዋ እና ተወዳጇ ዚነት ሙሃባ ጥቂት ልናካፍላችሁ ወደናል።
በ1959 ዓ/ም ደሴ ቁርቁር በተሰኘች አካባቢ ከሸህ ሙሃባ ይመርና ወ/ሮ ይመኑ ሙላት ቤት ደስታ ሆነ። ሴት ልጅ ይፈልጉ ለነበሩት እመት ይመኑ ባሰሙት ፀሉት ባደረሱት ስለት ከ12 ወንድ ልጆች በኋላ 13ኛ ልጃቸው ተወለደች።
ኋላ ከ1970ዎቹ መጨረሻ እስከ 80ዎቹ መጀመሪ በሙዚቃዋ ኮከብ ሆና ልታበራ ዘኒት ሙሃባ ተወለደች።
ማንጎራጎርን ገና በማህፀን ሳለች ከእናቷ የወረሰችው ዘኒት በአፍላ እድሜዋ ቀጠለችበት። የቤት ስራዋን ስትሰራ፣ ተልካም በየመንገዱ ማንጎራጎር የዘኒት መለያዋ ሆነ።
በአንዱ ደገኛ ቀን ደሴ ፒያሳ ላይ ቀይ መብራት አካባቢ ባለ አንድ ሆቴል የቦረና ሙዚቃ ስትጫወት በሰሙ የባህል አምባ ሰዎች አይን ላይ አረፈች። በዛች ቀን በድምፇ የተማረኩት የባህል አምባው መለማዮች የላሊበላ የባህል ቡድንን እንድቀላቀል ጠሯት።
የልጅንት ህልሟ ነበርና አላንገራገረችም። በተዛዋዣነት የባህል ቡድኑ አባለ ሆነች። የመጀመሪያ ስራዋንም በወቅቱ ይከበር በነበረው የአብዮት በዓል ቀን በአደባባይ አቀረበች።
ቀድሞም ጥሪዋ ለዘፋኝነት ነበርና በዚሁ የባህል ቡድን አዘጋጅነት
ይቀርብ የነበረው ሳምንታዊው የዝክረ ኪነጥበብ ፕሮግራም ላይ ታቀነቅን ጀመር።
ዘመን አይሽሬዎቹን አነ"ከምበል ደፋ"ን በዚህ መድረክ በማቅረብ ነገሰች። በድምፇ የተማረኩ ደግመው ደጋግመው "ቢስ ቢስ" አሉ።
እንደው ከምበልን ጨምሮ ስምንት አዳዲስ ስራዎቿን በዚህ መድረክ ለታዳሚያን ስታቀርብ ቆየች።
"እንደው ከንበል"
እንደው ከንበል እንደው ዘመም
እንደው ከንበል ይላል ጎፈሬው
ወጥቶ እስኪመለስ ልቤማ አያምነው x2
መንገደኛው ልቤ መንገደኛ ወዶ
ከማያቀው ሃገር ተሻገረ ማዶ አይ ማዶ
ቀንም ስራ አልሰራ እረፍት የለኝ ማታ አይ ማታ
ከሆዴ ተቋጥሮ የሩቅ ሰው ትዝታ ትዝታ
ሃሳብ ሳጠነጥን ስቋጥር ስፈታ ስፈታ
ሙሉ ሊንክ❤
የሙዚቃው አዘጋጅ ዳምጤ መኮንን የስራዎቹን መወደድ ሲረዳ ከስምንቱ ሙዚቃዎች ላይ ሌሎች ኹለት አዲስ ሙዚቃዎችን በመጨመር በማራቶን ሙዚቃ ቤት በኩል እንዲታተም ተደረግ። ይሄም የመጀመሪያዋ ካሴት ሆነ።
ሙዚቀኛውን በማበረታታት የሚታወቁት የማራቶን ሙዚቃ ባለቤት አቶ ታምሬ ውል ያሰፈረሙበትን ክፍያ በእጥፍ አሳድገው ለግጥም ለዜማ እና ለድምፅ ለአያንዳንዱ በወቅቱ 3000 ብር እንደከፈሉ ይነገራል።
የዚነት ሙዚቃዎች ምንጩ ያደገችበት ወሎ ግጥሞቹም ፍቅር ከሚቀምስበት የእረኛው መስክና የጉብሏ ውሃ ምንጭ ነው። ለዛዋ አድማጯን ማረከ። በየቦታው ዚነት ነገሰች። የ9ብሩ ካሴት 60ብር እስኪሸጥ ደረሰ።
"የአርሶ አደር ልጅ ነኝ"
እቴ ምላስ ጉልበቱ
አትፎግሪኝ በጠዋቱ
የአርሶ አደር ልጅ ነኝ የደገኛ የደገኛ x2
በስንዴ ለውጪኝ ካንቺው ማኛ ካንቺው ማኛ
አንቺ ቆለኛ x2
የማነህ ብልጣብልጥ ቆዳህ ሞኝ መሳይ x2
ምነወ መቸኮልክ ከወቀጣው ላይ
ቅድሚያ በገበያው ተስማምተናል ወይ
ቆለና ደገኛ መባባሉን ትተን
ያለሽን ያለኝን ባንድ ላይ አስማምተን
ነጩን ጤፍ እንጀራ ስንዴውን ዳቦ አርገን
ብንበላ ይሻላል ባንድ ላይ ተስማምተን
ሙሉ ሊንክ❤
ልጅነቷን ለቀረፀች ማንነቷን ላበጀች ሙዚቃ ራሷን ሰጠች። አልበጀም። ለሙዚቃ ያላት ፍቅር እና ትዳሯ እዚህና እዛ ተፋጠጡ። ልታስታርቅ ብትጥርም አልተሳካም። አደላች። መረጠች። ተረታች። ለሙዚቃ።
ከዚህ በኋላ ኮከብ ሆና የወጣችበት የወሎ ላሊበላ የባህል ቡድን በተለያየ ምክንያት ተዳከመ። ዚነትም በፅኑ ታመመች። የሁለተኛ አልበሟን ህዝብ እንዴት እንደተቀበለው ሳትሰማ አለፈች። አረፈች። ሳትጠገብ ተለየች።
ስንብትህ ይመር ትለናለች እንግዲ በዚያ ተስረቅራቂ ድምጿ
እንኳን ሆንኩህ እንጂ ካሰብክለት ማደር
መሄዱን ስታስብ መብት የለኝ አላስቀር x2
ባይሆን ግፉን ፈርተህ ስንብትህ ይመር
ስንብትህ ይመር
በውድ ሃገር ፍቅር ዋጋ አለው
ጣል ጣል ናቅ ናቅ ሳታረገው
አሰር ጠበቅ አርገህ ሳታረክሰው
ሚዛኑ ሚስጥር ነው አትሸንሽነው
ወይ ወረት ወይ ወረት
አይ ወረት x2
ሙሉውን ለምትሹ❤
ዚነት ሙሃባ በሰጠችን ጥቂት ግን ደግሞ ጣፋጭ ሙዚቃዎች ሁሌም አብራን ትኖራለች።
የኔ ናፍቆት የተሰኘውን ውብ መዚቃ ደግሞ በመቀጠል ተጋበዙልን😍
የኔ ናፍቆት ፍቅሬ ነህ ህይወቴ
ባንተ መውደድ ሳስቷል ሰውነቴ
መውደድ ፍቅር ብቅ በል በሞቴ
ፍቅሬ እባክህ ናልኝ
መውደድ ናፍቆትህ ጎዳኝ
እኔስ መሞቴ ነው ብትመጣልኝ ምነው
ያንተስ የብቻው ነው
ጋራ ሸንተረሩን ዞረህ ልቤን ሰንጥቀህ የሄድከው
በውበትህ አማለህ ወለላ የኔ ህይወት አንተ የሩቅ ሰው
ልቃኝህ በሃሳቤ በትዝታህ
ሙሉ ሊንክ👇
አንተ ልጅ ናልኝ በተሰኘው ውብ ሙዚቃዋ የዛሬው አይሬ ፕሮግራም እንቋጫለን።
አንተ ልጅ ናልኝ አንተ ልጅ ናልኝ
ፍቅሬ እባክህ ናልኝ
የልቤ የልቤ
ከቶ በምን ቋንቋ ልግለፀው መውደዴን
እባካችሁ ሰዎች እባካችሁ
ያንን ልጅ አማልዱኝ ለፍቅር ብላችሁ
እባካችሁ
ያንን ልጅ አማልዱኝ ዘመድ ወዳጆቹ
አድራሻውን ስጡኝ የቅርብ ጓደኞቹ
መሉውን ሊንክ ለምትሹ👇
ምንጮቻችን አማራ ማስ ሚዲያ ሸገር ራዲዮ ስንክሳር ፕሮግራም እና ዮቲዮብ ናቸው። 🙏
ቤተሰብ ያልሆናችሁ ተቀላቀሉን @Chobe2020 ለወዳጅ ዘመድም አዳርሱ።
አብራቹን ስለቆያቹ እናመሰግናለን።
ብሩህ ምሽት።
💃💃💚💛❤
Share this Scrolly Tale with your friends.
A Scrolly Tale is a new way to read Twitter threads with a more visually immersive experience.
Discover more beautiful Scrolly Tales like this.
