ህብረ ትርኢት Profile picture
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

Sep 27, 2020, 5 tweets

ውድ ቤተሰቦቻችን መስቀል እንዴት እያለፈ ነው?

ዛሬ ወዲህ ክርስትያን ቤተሰቦቻችን መስቀል በዓልን የሚያከብሩበት ወዲህ ደግሞ የሙዚቃ ንጉሳችን ጥላሁን ገሰሰ የልደት ቀኑ የሚታሰብበት ድርብ በዓል ነው። ለንጉሳችን ካለበት ከገነት አጸድ የእንኳን

ተወለድክ መልዕክታችን እንዲደርሰው ከተጫወታቸው ሙዚቃዎች ጥቂቶችን እየሰማን እናስበዋለን። የመጀመሪያችን የምናደርገው "የጠላሽ ይጠላ"ን ነው።

ፍቅሬ ሆይ ልንገርሽ ምንም ይሁን ምንም
እዚህ ቦታ ቀራት ቢሉኝ እኔ አላምንም

የልቤ ልግለፀው እውነት በሆነ ቃል
ተፈጥሮሽ ፍፁም ነው ውበትሽ ይደነቃል
ፍቅሬ ሆይ ልንገርሽ እኔ ምፈልገው
በክፋ የሚያይሽን እንዳያይ ያድርግው

እንደጠፋ አሳት ነው እንደተዳፈነ
ውበትሽን እያየ አይኑን የጨፈነ

የጠላሽ ይጠላ ብድሩ ይድረሰው
የጎዳሽ ይጎዳ ተፈጥሮ ትውቀሰው

ቁም ነገርሽን አይቶ የማያደንቅ ሰው
በግልፅ ያስታውቃል ችሎታ እንዳነሰው
የጠላሽ ይጠላ ይጠላ ብድሩን ይድረሰው
የጎዳሽ ይጎዳ ይጎዳ ተፈጥሮ ትውቀሰው

በከንቱ የሚያማሽ ስምሽን የሚያነሳ
ክፉ በመሆኑ አለበት ወቀሳ
መንገድሽ እየዘጋ በቅናት ተውጦ
ፀፀት ያንገብግበው ይኑር ተበጥብጦ

Share this Scrolly Tale with your friends.

A Scrolly Tale is a new way to read Twitter threads with a more visually immersive experience.
Discover more beautiful Scrolly Tales like this.

Keep scrolling