ህብረ ትርኢት Profile picture
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

Sep 27, 2020, 6 tweets

"በባይተዋር ጎጆ" ደግሞ ከጥላሁን ገሠሠ በጣም ከሚደነቅለት የፍቅር ዘፈኖቹ ውስጥ ደግሞ።

እያንዳንዱ ስንኝ ያዘለው ተማፅኖ ናፍቆት ስስት እና ፍቅር አጃይብ ያስብላል ❣️❣️❣️

በባይተዋር ጎጆ በባይተዋር አልጋ
እንግዲህ ለሊቱ ዋ እንዴት ይንጋ

ያረፈብሽ ክንዴ አሀ ያለበስኩሽ ኩታ
ያደርንበት ጎጆ አሀ ያሞቀን መኝታ
ሀቄን ይግለፅልሽ አሀ የፍቅሬን ሁኔታ
የኔ አካል እባክሽ እባክሽ
የኔ አካል እባክሽ በሞቴ
አልቋል ሰውነቴ በሞቴ

ሰውነቴ አልረሳ ብሎ አካል ሰውነትሽን
አካል ሰውነትሽን
ሰውነቴ ሲያሰላስል ያድራል ትዝታ ናፍቆትሽን
ትዝታ ናፍቆትክን
ሰውነቴ በሞቴ ይበቃል ጭንቀቴ

አለኝታዬ አድርጌሽ የመኖሬ ጥላ
ስልሽ እንደነበር የጭንቄ ከለላ
ምንም አልፈልግ እኔስ ካንቺ ሌላ
የኔ አካል እባክሽ እባክሽ
ይበቃል እባክሽ በሞቴ
አልቋል ሰውነቴ በሞቴ

ሰውነቴ ያንቺን ፍቅር ብቻ እያሰላሰለ
እያሰላሰለ
ሰውነቴ አረገኝ ብቸኛ አስታዋሽ የሌለው
አስታዋሽ የሌለው

ሰውነቴ በሞቴ
ይበቃል ጉዳቴ

Share this Scrolly Tale with your friends.

A Scrolly Tale is a new way to read Twitter threads with a more visually immersive experience.
Discover more beautiful Scrolly Tales like this.

Keep scrolling