ህብረ ትርኢት Profile picture
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

Sep 27, 2020, 7 tweets

ወዳጆች ይህንን የጥላሁን ገሠሠ "አምሳሉ" የተሰኘ ሙዚቃ ስራ ታውቁ ኖርዋል?

አንዲት ወዳጃችን ስሜ ይቆይ ብላ ይህንን ድንቅ ሙዚቃ አቀብላናለች። እግዜር ይክብርልን ብለናል።

ለኛም ይሄ የመጨረሻው ሙዚቃችን ይሆናል ለዛሬ

ግጥሙን ልብ በሉ 💚💛❤️

አበባው ለምለሙ ዛፉ ሳሩ ቅጠሉ
በፍጥረት አለም ላይ አምሮ የሚታይ ሁሉ
ውብ የሆነው ነገር የሚያምረው በሙሉ
ሀሩ ቀጭን ኩታው ለጌጥ እንቁና ሉሉ

የወርቅ የአልማዝ መስቀሉ እና ጥርባን ስራው በሙሉ
ጨዋነት ደግነቱ እና ቁም ነገሩ በሙሉ
ምንም ነገር ሳይቀረው መልኩ ያንቺ እኮ ነው አምሳሉ

ተራራው ፏፏቴው መስኩ ደኑና ጭቃው
የቀስተደመናው ቀለም ብሩህ ጨረቃው
ሳቅና ፈገግታው ፍቅርና ስሜቱ
የሰው ሰውነቱ ክብሩና ጌትነቱ

ካባ ጃኖው ቀሚሱ እና የአንገት ጌጡ ሀብሉ
ለህይወት የሚጠቅም ብዙ መልካም ነገር ሁሉ
ምንም ነገር ሳይቀረው መልኩ ያንቺ እኮ ነው አምሳሉ

ካንቺ ጋር አብሮ መዋል ህይወትን ለማደስ
በጣም ደስ ያሰኛል ለልብ ያነቃል መንፈስ
ፈገግታሽ ሐኪም ነው ህመምን ያድናል
ፍቅርሽ ደጋፊ ነው ሊይዝ ልብ ይጠግናል
የህይወት ጥብቅ ሚስጥሩ እና የደስታ ትርጉሙ ሁሉ

ውበትም ስሜትም ፍቅርም ብቻ እኮ ነው ይላሉ
ታዲያ ፍቅር እንዲሆን መልኩ ያንቺ እኮ ነው አምሳሉ

የፍቅር ውሉ ስሜቱ ሁሉ ነሽ አምሳሉ
የፍቅር ውሉ ስሜቱ ሁሉ ነሽ አምሳሉ

Share this Scrolly Tale with your friends.

A Scrolly Tale is a new way to read Twitter threads with a more visually immersive experience.
Discover more beautiful Scrolly Tales like this.

Keep scrolling