Adanech Abiebie Profile picture
Mayor - Addis Ababa

Nov 9, 2021, 5 tweets

ዛሬ ማለዳ ከጀግኖች አዉድማ ግምባር ተገኝተናል!!
በስፍራዉ በጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችንና በልዩ ሀይሎቻችን ላይ የሚታየው እልህና ወኔ፤ ኢትዮጵያዊ አይበገሬነት እጅግ አኩርቶኛል። 1/5

በተለይም በሴት እህቶቻችን የሰራዊቱ አባላት ላይ የሚታየው የስነልቦና ጥንካሬና ብርታት ልዩ ነዉ። 2/5

ከጀግኖች ጋር መዋል በራሱ ትልቅ ክብር ነዉ፤ ለኢትዮጵያችን ሉዓላዊነትና ለሕዝቦቿ ክብር ህይወታቸውን ሳይሰስቱ ከሰጡን ብርቅዬ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ጋር በጀግኖች መገኛ አብሮ መሆን ደግሞ ድርብርብ ሀሴትና ... 3/5

ተጨማሪ አገርንና ሕዝቦቿን የማገልገል፤ የመዉደድና የማክበር አንዳች ምትሀታዊ ስሜት ይፈጥራል። 🇪🇹ን ለማዳን ተመን የሌለውን ህይወት እየሰጡ ታላቅ ድል እያስመዘገቡ ላሉት ጀግኖች ተከፍሎ ስለማያልቀው ድንቅ ውለታቸው ዝቅ ብለን አመስግነናቸዋል።4/5

ሀገር ለማፍረስ የመጣውን አሸባሪው የህውሐት ቡድንን በመፋለሙ ተግባር ብቻቸውን አለመሆናቸውንና የኢትዮጵያ ልጆች ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ህይወትም ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠንላቸዋል።
#ኢትዮጵያታሸንፋለች እኔም የኢትዮጵያ ወታደር ነኝ!5/5

Share this Scrolly Tale with your friends.

A Scrolly Tale is a new way to read Twitter threads with a more visually immersive experience.
Discover more beautiful Scrolly Tales like this.

Keep scrolling