My Authors
Read all threads
THREAD
(1/12) ሰለሞን እባላለሁ! “ሰው” የሚለው ፍጹም የሚገልጸኝና ሙሉነት የሚሰጠኝ ማንነት ነው! ነገር ግን ሰው ከመሆን ቀጥሎ ማንነት የምጠየቅ ከሆነ ኢትዮጵያዊ ከማለት ውጭ ምን ልል እችላለሁ?...
(2/12) ሰው ከመሆን ቀጥሎ መርጬ ሳይሆን ፎንቃ🙂የሚባለው ክስተት በፈጠረው አጋጣሚ አማራም፣ ኦሮሞም፣ ትግሬም ያለበት ኢትዮጵያዊ ሆኜ ተወልጃለሁ። ላብራራ! ከዕለታት አንድ ቀን፣ አማራ ሴት አያቴ ከትግሬ ወንድ አያቴ በፍቅር ወድቀው አባቴን ወለዱ…
(3/12) ሁለቱ ኦሮሞ አያቶቼ ደግሞ በፍቅር ወደቁና እናቴን ወለዱ። ግማሽ ከአማራና ግማሽ ከትግሬ የሆነው ኢትዮጵያዊ አባቴ ደግሞ ከኢትዮጵያዊቷ ኦሮሞ እናቴ ፍቅር ይዞት እኔ ተወለድኩ። ታዲያ እኔ ራሴን #ኢትዮጵያዊ እንጂ ማን ብዬ ልጠራ እችላለሁ?...
(4/12) ልክ እንደእኔ ከተለያየ ዘር (ጉራጌ፣ ከምባታ፣ ሲዳማ፣ ሃዲያ፣ ጋምቤላ፣ ወላይታ፣ ሃረሬ፣ ሶማሌ እና ሌሎችም…) የሚወለዱ ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን አሉ… ከቤተሰቤ የምወደው ነገር ቢኖር፣ ምን ያህል ሰው መሆን በራሱ በቂ እንደሆነ እና…
(5/12) እንዲሁም ኢትዮጵያዊነት ውስጤ እንዲሰርጽ የተጫወቱት ሚና ነው! ከአምቦ የሆነችው ኦሮሞዋ እናቴ በኢትዮጵያዊነቷ ትኮራለች፤ እንዲሁም ግማሽ ትግሬና ግማሽ አማራው አባቴ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ነበር! እናም ዘረኝነት ለኔ ባዕድ ነው!...
(6/12) ይገባኛል አሁን የምናልፍበት መከራ፣ ወንድም በወንድሙ ላይ መነሳቱ፣ ዘር እየለዩ መጋደሉ እጅግ የሚያስጨንቅ ነው። በዚህ የሸለቆ ጉዞ ውስጥም እያለፍን መፍትሄው ኢትዮጵያዊነትን በማጉላት በአብሮነት መኖር ነውና አንድ ነገር እናድርግ።...
(7/12) ከተቀላቀለ ዘር የመጣችሁ በፍጹም ድፍረት ኢትዮጵያዊነታችሁን አውጁ! ከአንድ ዘር የምትመዘዙ ወንድምና እህቶቻችንም ኢትዮጵያዊነታችሁን በማስቀደም ይህንን አላማ ተቀላቀሉ! #ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊ/ት እና #ኢትዮጵያዊነት ሃሽ ታጎችን ይጠቀሙ…
(8/12) የኔ ትውልድ በዘር መከፋፈል ሳይሆን በበጎ ሃሳቦች ላይ የተመሰረተ የሃገራችንን በጎ ዕጣ ፈንታ ለመፈጸም ይነሳል። ከኋላችን ጥለን ያለፍነው ታሪክ (እውነቱም/ውሸቱም፣ ውቡም/አስቀያሚውም፣ ጥሩውም/መጥፎውም) እንማርበታለን እንጂ አንቀይረውም…
(9/12) ስላለፈው ታሪክ ላለመስማማት እንስማማ ለነገአችን ምንም ስለማይፈይድልን! ንጹህ ገጾች ያሉት ደብተር ፊታችን ቁጭ ብሎ ለምን ያለፈ ታሪክ የተጻፈበት መጽሃፍ ላይ ደርበን በመጻፍ ያለፈን ታሪክ የመቀየር የማይቻል ሙከራ ለማድረግ እንደክማለን?…
(10/12) እመኑኝ፣ ጽሁፍ ባለበት የመጽሃፍ ገጽ ላይ በጥቁር ብዕር ደርቦ መጻፍ የድሮውንም ጽሁፍ ማጥፋት እንዲሁም አዲስ ለመጻፍ የተሞከረውንም ማንበብ ያለመቻል ዝብርቅርቅ ከንቱ ሂደት ማለት ነው።...
(11/12) ከኋላውም ከወደፊቱም አልባ ሆኖ ኪሳራ ውስጥ ከመግባት አዲስ ታሪክ በመጻፍ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሆን ብሩህ ነገአችንን እንፍጠር!💚💛❤️ ...
(12/12) በዚሁ አጋጣሚ፣ "እኔ ላይ እስካልደረሰ" በሚል በዝምታ ላይ ያለው ብዙሃኑ ህዝብ፣ እንዲሁም ሚዛናዊ እይታን ማሳየት የሚችል ብሩህ አዕምሮ ያለው ሁሉ ሃገርን ከፅንፈኛ ዘረኝነት ለማዳን ዛሬ ላይ ከመቼውም በላይ ይፈለጋሉ!
Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh.

Keep Current with Solomon Kassa

Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

Twitter may remove this content at anytime, convert it as a PDF, save and print for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video

1) Follow Thread Reader App on Twitter so you can easily mention us!

2) Go to a Twitter thread (series of Tweets by the same owner) and mention us with a keyword "unroll" @threadreaderapp unroll

You can practice here first or read more on our help page!

Follow Us on Twitter!

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3.00/month or $30.00/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!