Thread 1
ይህ ቅጥልጥል በአሳዛኝ ሁኔታ የኢትዮጵያ የስልጣኔ መሰረት የሆኑትን ሰሜን ኢትዮጵያውያንን አፋጅቶ ለማዳከም በ "ብልጽግና ወንጌል" ፖለቲካዊ የሀይማኖት ርእዮተ ዓለም በ @AbiyAhmedAli ጦርነት ሰለታወጀበት የኢትዮጵያ ክፍል #ትግራይ ነው Image
Thread 2
እኛ ኢትዮጵያዊያን የ3ሺ ዘመን ታሪክ አለን ብለን የምንመጻደቅበት አክሱም ፣ የኢትዮጵያ ስርወ መንግስት አሰራር (State Craft) እና የስልጣን ተዋረድ (Hierarchy) ጥንስሱ የተጀመረበት የማንነታችን መነሻ ያለው አክሱም ትግራይ ነው። Image
Thread 3
ከአውሮፓውያን ቀድማ ከአብርሀማዊ እምነቶች አንዱ የሆነውን ክርስትናን የተቀበለችው ኢትዮጵያ ለመሆኗ የምትመስክር በኢትዮጵያ ተዋሕዶ አማኞች እንደሚታመነው አምላክ ለሙሴ የስጠው የአስርቱ ትእዛዛት ጽላት ያረፈበት አክሱም ትግራይ ነው። ImageImage
Thread 4
ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በተቃዋሚዎቻቸው ቢሳደዱ "ወደ ኢትዮጵያ ሂዱ" ብለው ተከታዮቻቸውን ወደ ሀገራችን ሲልኩ ተከታዮቻቸው የመጡት ወደ ነጃሺ (ውቅሮ)ትግራይ ነው። ይህ ትግራይ ለኢትዮጵያ የክርስትናም የእስልምናም መስረት መሆኗን ያሳያል ImageImage
Thread 4
እኛ ኢትዮጵያዊያን ስለኛ የማያውቅ ባእድ በየትም ቦታ ባገኘን ቁጥር ቀድመን የምንፎክርበት የነጻ ህዝብነታችና ኩራታችን ምልክት የሆነው ቅኝ ገዥዎችን ድባቅ የመታንበት የአድዋ ሶሎዳ ተራሮች የሚገኙት በትግራይ ነው። ImageImageImage
Thread 5
ጠላትን ድባቅ መምታት ካነሳን በኩፊት ግብጻውያንን በሰሐጢና ዶጋሊ ኢጣልያዊያንን እየደጋገመ የረታው የተምቤኑ ትግራይ ኢትዮጵያዊ አሉላ አባነጋ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም ወደር የማይገኝለት የጦር አበጋዝ መሆኑን አስመስክሯል። ImageImageImage
Thread 6
ባለ ግርማ ሞገሶቹ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ምሽጎች የመልክዐ ምድር ተአምርነት የሚታይባቸው የገረሀልታ ተራሮች የሚገኙት በትግራይ ነው። ImageImageImage
Thread 7
ስለ ተራራ ከተነሳ ዘጠኝ የመካከለኛው ምስራቅ ክርስቲያን ባህታዊ መነኮሳት በቀኖና (doctrine) ምክንያት ከየሀገሮቻቸው ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ ቢመጡ ፣ ተከብረው ተቀድሰው አቡነ አረጋዊ ፣ አቡነ የማታ የሚል ኢትዮጵያዊ ስም ተሰቷቸው... ImageImageImage
Thread 8
አስደናቂ አብያተ ክርስትያኖቻቸውን ገንብተው የኖሩት በትግራይ ነው። እነዚህ አብያተ እምነቶች። ለኢትዮጵያ የእምነት ፣ የጽናት ፣ የሀገር እና የአምላክ ፍቅር ምንጮች ሆነው ለዘመናት አገልግለዋል። ImageImage
Thread 9
የትግራይ ህዝብ ውብ ፣ ደግ ፣ ሀይማኖተኛ ፣ እንግዳ ተቀባይ በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ መስራችንቱም የሚኮራ በራሱ የሚተማመን ኢትዮጵያን መሬቷን ብቻ ሳይሆን በመሬቷ የሚኖሩትንም ህዝቦች ሁሉ የሚወድ ድንቅ ህዝብ ነው። ImageImageImageImage
Thread 10
ትግራይ በልጅነታቸው እውቀትን ፍለጋ በመርከብ ተደብቀው ወደ አውሮፓ የሄዱት ፣ በፈረንሳይ በ18መቶዎቹ የመጀመርያው ጥቁር የዩኒቨርስቲ መምህር የነበሩት "ሀገሬን" ብለው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት የገብረህይወት ባይከዳኝ የትውልድ ቦታ ናት ImageImage
Thread 11
ዛሬ ይህ ህዝብ ተገፍቶ ተነጥሎ በትእቢት በተሞላ ፣ በባእዳዊ ርእዮተ አለም እየተገፋ ጽናቱን ፣ እምነቱን ማንነቱን እየተፈታተነው ባለ እኩይ መሪ @AbiyAhmedAli ፍጹም ፍትሐዊ ባልሆነ መልኩ ጦርነት ታውጆበት በከበባ (under siege) ነው ያለው Image
Thrrad 12
የዚህ እኩይ ወረራና የታቀደ ፋሽስታዊ ጭፍጭፋ ምክንያት በክልሉ ያለ በህዝቡ የተመረጠ መንግስት ለዚሁ አላዋቂ ጨካኝና አጭበርባሪ መሪ አሽከርነት ለመግባት አሻፈረኝ ማለቱ ነው።
Thread 13
ምንም እንኳን ህወሓት እጅግ በርካት ጥፋቶች በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ከህወሓት በእጥፍ ወንጀል እየፈጸመ ያለው፣ ለብዙሐን ህይወት መጥፋትና መፈናቀል ምክንያት የሆነው @AbiyAhmedAli ማንንም በጥፋት..
Thread 14
የመወንጀል የሞራል ብቃት የለውም። ባለፉት ከሁለት አመታት በላይ ኢትዮጵያዊያን ፍጹም በሆነ ሰላም ሰውነታቸው ተከብሮ ሳይተነኮሱ በሰላም ትምህርታቸውንም ሆነ ስራቸውን በሰላም ይከውኑበት የነበረ ክልል የትግራይ ነው። Image
Thread 15
በብዙ የኢትዮጵያ ክፍል የአማራ ተወላጆች በአሰቃቂ ሁኔታ ኢሰብአብአዊ በሆነ መንገድ ሲግደሉ ፣ ሰውነታቸው ብቻ ሳይሆን ፣ ኢትዮጵያዊነታቸውም ተከብሮ ትምህርታቸውና ስራቸው ሳይስተጓጎል ከኖሩበት ጥቂት ቦታዎች መካከል ትግራይ አንዱ ነው
Thread 16
ዛሬ "የ3ሺ ዘመን ታሪኬ" "አባቶቼ በአድዋ ድል ቅኝ ገዥዎችን ድል ያደረጉት" እያሉ የሚንቀባረሩት በሌላ በኩል ትግራይ ላይ "ጦር አውርድ" እያሉ የሚያቅራሩት "ኢትዮጵያውያን" ህዝቡን ከነ መሬቱ እንጂ መሬቱን ብቻ መውደድ እንደማይቻል ይወቁት።
Thread 17
ህወሓት ለትግራይ ህዝብ ይበጀው አይበጀው መራጩ የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው። በግድ እገዛሀለው ለሚሉትን ግን ግን የትግራይ ህዝብ የሚያነጋግርበት የራሱ ቋንቋ አለው። በዚያም ቋንቋ ሳይወዱ በግድ ደጋግሞ ላስግብርህ ያሉትን አሳምኗል
Thread 18
ዛሬ ለአብይ አህመድ አሽከርነት ብለው ኢትዮጵያን የመሰረቱ ሰሜን ኢትዮጵያዊያንን (አማራና ትግራይ) እያፋጁ አማራው በተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል እንደበግ እየታረደ እያዩ እንዳለየ ያለፉ የአማራ ባለስልጣናት ጊዜው ሲደርስ ለህግ ይቀርባሉ። ImageImageImageImage
@threadreaderapp please unroll. Thank you!

• • •

Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh
 

Keep Current with Naty Yifru (ናቲ ይፍሩ)

Naty Yifru (ናቲ ይፍሩ) Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

PDF

Twitter may remove this content at anytime! Save it as PDF for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video
  1. Follow @ThreadReaderApp to mention us!

  2. From a Twitter thread mention us with a keyword "unroll"
@threadreaderapp unroll

Practice here first or read more on our help page!

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3/month or $30/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!

Follow Us on Twitter!