1/11
#ፈታ_እንበል 😅

ሰሞኑን ሰው ሁሉ በ19 ሚሊዮን ብር ስለተገዛው አዲሱ ባስ ሲያወራ ለምን ሄጄበት አልሞክረውም ብዬ ዛሬ ከጀሞ ወደ ሜክሲኮ ሄጄ ነበር።
...
ባስ ስቴሽኑ ጋ የደረስኩት ከጠዋቱ 12 ሰአት ሲሆን ከተደረደሩት ውስጥ አንዱን መርጩ ገባሁ
2/11
በር ላይ ሚኒ ስከርት የለበሰች አስተናጋጅ በፈገግታ ተቀብላኝ ጉንጬን ከሳመችኝ በኋላ ስልኳን ሰጥታኝ ወደ ውስጥ አስገብታ ወንበር አስያዘችኝ።
...
m.facebook.com/story.php?stor…
3/11
በጣም ብርድ ስለነበር ከወንበሬ አጠገብ የነበረውን Heat የሚለውን በተን ክሊክ ሳደርገው ወዲያውን ከወንበሬ ዙሪያ ጠርዝ ላይ ነጭ ጋቢ ወጥቶ ሙሉ ሰውነቴን አለበሰው።
4/11
በዚህ ተገርሜ እንደምንም ከጋቢ ውስጥ እጄን አውጥቼ ፊት ለፊቴ ያለውን ስክሪን ሳበራው መኪናው ላይ ስለተገጠሙት ቴክኖሎጂዎች የሚገልፅ ፅሁፍ መጣልኝ።
...
5/11
ፅሁፍ ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ ክረምት ላይ መንገዶች በጎርፍ ሲሞሉ ወዲያውን ቅርፁን ወደ ዝርግነት በመቀየር ወደ መርከብነት የሚለወጥ ሲሆን በውስጡም መለስተኛ ኳስ ሜዳና የባስኬት ቦል ኮርቶች እንዲሁም ለፈረስ ግልቢያ የሚሆን ሰፊ ሜዳ ይዟል።
6/11
ምናልባት ከቤቱ ተቻኮሎ ፊቱን ሳይታጠብ የመጣ ተሳፋሪ ካለ የራሱን የፊት ሳሙናና የጥርስ ብሩሽ ከኮልጌት ጋር እና ከማይመለስ አንድ ፎጣ ጋር የሚያቀርብ ሲሆን ስቲምና ሳውናም ከሾፌሩ ጀርባ ባለው ክፍል ውስጥ ዝግጁ ሆኖ ተሳፋሪዎቹን ይጠብቃል
7/11
በተጨማሪም መንገድ በሚዘጋበት ጊዜ ከጎን እና ከጎን ክንፎቹን በመዘርጋት ልክ እንደ ዴር 33 ከራዳር እይታ ውጪ መብረር የሚችል ሲሆን ምናልባት በሰማይ ላይ እያለ የሰማይ ትራፊክ መጨናነቅ ቢያጋጥመው እንኳን ከስሩ እሳት በመፍጠር ራሱን ...
8/11
... ወደ መንኮራኩነት በመቀየር ወደ ጨረቃ የሚያምዘገዝግ የሮኬት ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።
...
ለባለስልጣኖች ራሱን የቻለ መኝታ ቤት ያለው ሲሆን ለሰፊው ህዝብ ደግሞ ትኬት ሳይቆርጥ የገባን ቆርጦ ከገባው የሚለይ ሴንሰር ተገጥሞለታል።
9/11
የሚገርመው ትኬት ያልቆረጡትን ሰዎች በስም መለየት የሚችል ሲሆን አንዱ ተሳፋሪ ሳይቆርጥ ገብቶ ወዲያኑ "ደጀኔ እባክህ ወይ ቁረጥ ወይ ውረድ አትሞላፈጥ" በሚል ድምፅ ተሳፋሪውን ሲያስጠነቅቅ በጆሮዬ ሰምቻለሁ።
10/11
በመጨረሻም ሜክሲኮ ባስ ስቴሽን ደርሰን ስንወርድ ለሁላችንም የጫማ ማስጠረጊያ እና ለቀጣይ ታክሲ መሄጃ ስልሳ ስልሳ ብር የተሰጠን ሲሆን ሾፌሩን ጨምሮ ሁሉም የባሱ ሰራተኞች በእግራቸው የተወሰነ መንገድ ሸኝተውናል።
11/11
በእኔ እይታ ይሄ ባስ 19 ሚሊየን ሲያንስበት እንጂ ከዚህም በላይ ይገባዋል።

ዳጊ ነኝ ከገፈርሳ ወንዝ ማዶ

m.facebook.com/story.php?stor…

• • •

Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh
 

Keep Current with IYOBA 🇪🇹🇪🇷

IYOBA 🇪🇹🇪🇷 Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

PDF

Twitter may remove this content at anytime! Save it as PDF for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video
  1. Follow @ThreadReaderApp to mention us!

  2. From a Twitter thread mention us with a keyword "unroll"
@threadreaderapp unroll

Practice here first or read more on our help page!

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3/month or $30/year) and get exclusive features!

Become Premium

Don't want to be a Premium member but still want to support us?

Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal

Or Donate anonymously using crypto!

Ethereum

0xfe58350B80634f60Fa6Dc149a72b4DFbc17D341E copy

Bitcoin

3ATGMxNzCUFzxpMCHL5sWSt4DVtS8UqXpi copy

Thank you for your support!

Follow Us on Twitter!

:(