Tewodros Belay Profile picture
«ጆሮ ገንጣይ!» የሚሉኝ ብዙዎች ናቸው፤ ወሬ ከጀመርኩ ለሰው ጆሮ የመጠንቀቅ ልምድ ስላልፈጠረብኝ መሰለኝ፡፡ ጥሩነቱ «ጆሮ ገንጣይ» እንጂ «ሀገር ገንጣይ» አለመባሌ ነው፡፡ ;)
Apr 22, 2020 8 tweets 2 min read
የፋሲካ ዕለት የሆነ ነው፡፡ ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ በፓትሮል የሚንቀሳቀሱ የፖሊስ አባላት አስኮ አዲስ ሰፈር አከባቢ ያደረጉት ድርጊት አስገራሚ ነው፡፡የአከባቢው ነዋሪ እስከዚህ ሰዓት ድረስ ምን እንደተፈጠረ እንኳ የሚያስረዳው አላገኘም፡፡ 1/8 በድንገት በሰፈሩ የተገኙት የፖሊስ አባላት በመንገዱ ላይ ያገኙትን ነዋሪ በሙሉ እያገላበጡ በዱላ መደብደብ ጀመሩ፡፡ ድብደባቸው ከፋፋይ አልነበረም፡፡ ሴት፣ ወንድ፣ ወጣት፣ አዛውንት ሳይል ያገኙትን በሙሉ መቀጥቀጥ ጀመሩ፡፡ 2/8