Talk Ethiopia w/ Isaac ቶክ ኢትዮጵያ Profile picture
📣 ስለ ኢትዮጵያ 🇪🇹 ማኅበረ ፖለቲካ 🎬 ስለእኩልነት እና አካታችነት 💪🏿 "ኢትዮጵያ ለሁላችን ትሁን!"

May 7, 2021, 9 tweets

"እንዴት ሙስሊሙ በአደባባዩ ማፍጠር አይችልም ይላሉ?" ብለህ ገረመህ አይደል? አይግረምህ… ቤ/ክ መዋቅር ውስጥ አሁንም ሙስሊሙን እንደእንግዳ እንጂ እንደዜጋ የማይቆጥሩ ጥቂት ኋላቀሮች አሉ… በተለይ ደግሞ የማኅበሩ ሰዎች ይህ ዋና ሥራቸው ነው።👉

👉 ሙስሊሙ እና ኦርቶዶክሱ ሲተሳሰብ ጨጓራቸው የሚነሣባቸው ጽንፈኞች ናቸው።
በ2019 ሴፕቴምበር 2 በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት የጻፈውን ደብዳቤ ላስታውስህ… 👉

"…እንግዳ ቤቱን ካቀናው ባለቤት እኩል መሆን አይችልም እንዲህ በመሆኑም 1 ቀንም የምሬት ቃል አሰምታ የማታውቅ ቤ/ክ እኩልነት መቻቻል የሚለውን ቀይ መስመር ንደው የመጥፋቷን ነገር በሚመክሩ ሰዎች እየደረሰባት ያለው ግፍ በእጅጉ አሳዛኝ ነው…"

👉 እንዲህ ዓይነት ሙስሊሙን እንደእንግዳ የሚቆጥሩ ሰዎች መዋቅሩ ውስጥ ቢኖሩም አማኙ ግን ከጎንህ እንደሆነ አትዘንጋ… እሁድ አብረውህ በፍቅር እና በመተሳሰብ የሚያፈጥሩ ኦርቶዶክሳዊ ወንድም እኅቶችህ ብዙ ናቸው።👉

የእነሱን አጋርነት ከታች ባያያዝኩልህ ስክሪንሾቶች ተመልከት… ስዘዋወር ካገኘኋቸው ጥቂቶች አጋራሁህ እንጂ እጅግ ብዙ ናቸው…
.
#እሁድንበአብዮትአደባባይ

Share this Scrolly Tale with your friends.

A Scrolly Tale is a new way to read Twitter threads with a more visually immersive experience.
Discover more beautiful Scrolly Tales like this.

Keep scrolling