, 25 tweets, 3 min read Read on Twitter
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግለጫ

ውድ የጋራ ንቅናቄያችን ቤተሰቦች፤

በቅድሚያ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) በኢትዮጵያ ሕጋዊነት አግኝቶ መመዝገቡንና የዚህም ማረጋገጫ ሠርቲፊኬት መቀበሉን ስናበስርላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
እንደሚታወቀው የጋራ ንቅናቄያችን ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት በውጭ አገር (በአሜሪካ) ተመዝግቦ በሕጋዊነት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።
ሆኖም በአገራችን እየተካሄደ ካለው የለውጥ እንቅስቃሴ አኳያ በውጭ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ድርጅቶች አገር ውስጥ ገብተው በነጻነት እንዲሠሩ በመፈቀዱ ይህንን ተከትለን የጋራ ንቅናቄያችንን በሕጋዊነት ለማስመዝገብ ችለናል።
ይህም ደግሞ ለድርጅታችን ዓላማዎች በሕዝብ ዘንድ መስረጽ ዓይነተኛ አስተዋጽዖ የሚያደርግ ሲሆን ከሕዝባችንም ጋር ያለገደብ እንድንገናኝና በአገራችን ጉዳይ ላይ ተጽዕኖ እንድናመጣ በርካታ ዕድሎችን የሚከፍትልን ነው።
“ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ” (አኢጋን) ከየትኛውም የፖለቲካ ወገን ነፃ የሆነ በፍትህ፣ በሰላም፣ በዕርቅ፣ በርትዓዊ ፍትሕና በሰብዓዊ መብቶች መከበር ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራ የመብት ተሟጋች ድርጅት ነው።
ኢትዮጵያውያንን በአንድ ጥላ ሥር ለማምጣት አልሞ የሚሠራው ድርጅታችን ራሱን በሁለት አዕማዶች ላይ ተክሏል።
በዋናነት “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ!” የሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው የድርጅቱ አዕማድ ደግሞ “ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም!” የሚል ነው።
እነዚህን ግዙፍ መርሆዎች ተግባራዊ ለማድረግ የሚጠቀምባቸው ስልቶች ደግሞ ዓመጽ፣ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ምቀኝነት፣ ዘረኝነት፣ ወገንተኝነት፣ ወዘተ ሳይሆን ከከረረ ልዩነት፣ ዋልታ ረገጥነትና ድንበር አስማሪነት በጸዳ መልኩ ሰብዓዊ ዘርን፤
በጽኑ ፍቅር በማክበር፣ በመውደድና ለሌላው ሰው ከልብ በመነጨ ቅንነት በሚያስብ አመለካከት ላይ በመመሥረት ነው። የእነዚህ ተግባራት መዳረሻ ደግሞ በአገራችን ላይ ፍቅር፣ ሰላም፣ ኅብረት፣ ዕርቅና ርትዓዊ ፍትሕ (Restorative Justice) ማስፈን ነው።
የጋራ ንቅናቄያችን ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት በዓለምአቀፍ ደረጃ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን በቀዳሚነት በሦስት ዐቢይ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፤ እነዚህም፤ሕዝባዊ ጥብቅና (Advocacy)በመቆም የተቆርቋሪነት ድምጽ ማሰማት፤
በሰብዓዊ መብቶች መከበር (Human Rights) እና ግንዛቤ በማስጨበጥ (Awareness) እንዲሁም በማኅበረሰባችን ዘንድ የዕርቅና ርትዓዊ ፍትሕ መስፈን አስፈላጊነት ግንዛቤ በማስያዝ ናቸው።
በመስከረም ወር 2011ዓም የጋራ ንቅናቄያችን ልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ ጀምሮ በእነዚህ የንቅናቄው መርኾዎች ላይ በሰፊው ሲሠራ ቆይቷል።
ከከፍተኛ የፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣናትን በማነጋገር፣ በበርካታ የመንግሥትና የግል ሚዲያ ላይ በመቅረብ የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በማስረዳትና መፍትሔ በመጠቆም፤ እንዲሁም ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች (በተለይ የአገር ሽማግሌዎች፤
ከአባ ገዳዎች፤ ከጆካ (ጉራጌ)፤ ሐረሪና ሶማሊ ሽማግሌዎች) ጋር በመነጋገር ዘላቂነት ያለው ሰላም፣ ፍትሕ፣ ዕርቅ በአገራችን የሚሰፍንበትን መንገድ በተመለከተ ትምህርት ሲወስድና ግንዛቤ ሲያስጨብጥ ቆይቷል።
“ለመተማመን እንነጋገር”በሚል መሪ መፈክር ከመስከረም 2011ዓም እስከ ጥር ድረስ በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች በመገኘት ለአገራችን የሚጠቅሙና የጋራ ንቅናቄያችንን መሠረታዊ መመሪያዎችን በሕዝባችን እንዲሰርጹ ለማድረግ የሚቻለውን ሲሠራ ቆይቷል።
በአገራችን ሁሉም አቅጣጫዎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በመገኘትም በብዙ ሺህ ከሚቆጠሩ ተማሪዎች ጋር በመገናኘት ወጣቶች አዲሲቷን ኢትዮጵያን እንዴት መመሥረትና መገንባት እንዳለባቸው ግንዛቤ ሲያስጨብጥ ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም በየአካባቢው የሚነሱ ግጭቶችን በማርገብና ሌሎችም እንዳይነሱ በመከላከል በኩል የልዑካን ቡድናችን ተገቢውን ሚና ተጫውቷል ብለን እናምናለን።
በቅርቡ እንደገና ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት የጋራ ንቅናቄያችን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ላለፉት አምስት ሳምንታት በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውኑ ቆይተዋል።
ምንም እንኳን እርሳቸው በተመለሱበት ወቅት እጅግ አሳዛኝና ደም አፋሳሽ የሆነው ግድያ በመከሰቱ የኢንተርኔትና የስልክ መስመሮች እንዳይሠሩ ቢደረግም በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ በመጠቀም የሚከተሉትን አከናውነዋል፤
• ከኢቢሲ ጋር ለአንድ ሰዓት የቆየ የቴሌቪዥን ቃለምልልስ አድርገዋል፤ ይህም በድርጅቱ የምሽት ክፍለጊዜ እጅግ በርካታ ሚሊዮኖች በሚያዩት ሰዓት የቀረበ በመሆኑ የተሰጠው ሽፋን እጅግ ሰፊ ነበር፤
• ከዚህ ሌላ በአዲስ አበባና አካባቢው በሚገኙ የተለያዩ የሬዲዮ፣ የቲቪ እና የኅትመት ሚዲያ ውጤቶች ጋር ሰፋ ያለ ቃለምልልስ አድርገዋል፤
• በቅርቡ በድሬዳዋ የተካሄደውንና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የሚመራውን አዲስ ወግ ስብሰባ ላይ አስተባባሪ ተናጋሪ ሆነው በመቅረብ ንግግር አድርገዋል፤
• ከትምህርት ሚኒስቴርና ከሰላም ሚኒስቴር ጋር የአኢጋንን ዋና ዓዕማዶች በአገራችን ሕዝብ በተለይም በተማሪው ውስጥ ማስረጽ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ውይይትና ምክክር ተጀምሯል፤
• ባለፈው የተጀመረውን ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር የጋራ ንቅናቄያችን የሚያደርገውን ውይይት ስፋትና ጥልቀት ባለው መልኩ ለማካሄድ በየቦታው ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሚደረገው ግንኙነት ቀጥሏል፤
እነዚህንና አስቀድመን የጀመርነው “ለመተማመን እንነጋገር” መርሃግብር ለማስፈጸም የወገኖቻችንን ድጋፍ እንፈልጋለን።
Missing some Tweet in this thread?
You can try to force a refresh.

Like this thread? Get email updates or save it to PDF!

Subscribe to Obang Metho
Profile picture

Get real-time email alerts when new unrolls are available from this author!

This content may be removed anytime!

Twitter may remove this content at anytime, convert it as a PDF, save and print for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video

1) Follow Thread Reader App on Twitter so you can easily mention us!

2) Go to a Twitter thread (series of Tweets by the same owner) and mention us with a keyword "unroll" @threadreaderapp unroll

You can practice here first or read more on our help page!

Follow Us on Twitter!

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just three indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3.00/month or $30.00/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!