My Authors
Read all threads
Thread: ነውረኛ መነጽራችሁን አውልቁ!

1/ ሁሉንም ፀብ እና ችግር በሃይማኖት ማዕቀፍ መመልከት ለማናችንም አይጠቅምም። ለሚዲያ ማጥላያ ዘመቻ ይጠቅም ይሆናል። ለአገር ግን አይጠቅምም። 👇
2/ መንገድ ላይ አንድ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ሰው ሠርቆ ሲሮጥ ብታየው «አንድ ኦርቶዶክስ ሠርቆ ሲሮጥ አየሁ» ብለህ መናገር እጅግ ነውር ነው። ሃይማኖቱን ዒላማ ማድረግ ነው። ፍጽም ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ያፈነገጠ ነውር ነው። 👇
3/ መንገድ ላይ አንድ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ ሰው ሠርቆ ሲሮጥ ብታየው «አንድ ፕሮቴስታንት ሠርቆ ሲሮጥ አየሁ» ብለህ መናገር እጅግ ነውር ነው። ሃይማኖቱን ዒላማ ማድረግ ነው። ፍጽም ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት የማይጠበቅ ነውር ነው። 👇
4/ መንገድ ላይ አንድ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ሰው ሠርቆ ሲሮጥ ብታየው «አንድ ሙስሊም ሠርቆ ሲሮጥ አየሁ» ብለህ መናገር እጅግ ነውር ነው። ሃይማኖቱን ዒላማ ማድረግ ነው። ፍጹም ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት የማይጠበቅ ነውር ነው። 👇
5/ በቃ ነውር ነው! መንገድ ላይ አንድ ማተብ የለበሰ ሰው ሲያልፍ ጫማዬን ረግጦ ቢያቆሽሽብኝ «አንድ ኦርቶዶክስ ረገጠኝ» ብዬ ማሰብ ረኸጥነትና ደደብነት ነው። የድድብና ጥግ ነው። ሰው እንዲህ ማሰብ የለበትም! እንዲህ ብሎ መምከር ራሱኮ ያሳፍራል!👇
6/ ክስተቶችን ሁሉ በሃይማኖት መነጽር ማየት ፌር አይደለም። ለምሳሌ ፌስቡክ ላይ ሁሉም ይጽፋል ግን ከጸሐፊዎቹ ጀርባ ሃይማኖታቸውን ማየት ጤናማ አይደለም። ይህን መነጽር አይኑ ላይ የመለጎጠ ሰው አዕምሮ የሰይጣናዊ ሐሳቦች ማብላያ ነው የሚሆነው!👇
7/ እንዲህ ዓይነት ዕኩይ መነጽር ለብሰህ ከሰዎች ጀርባ ያለውን ሃይማኖት እያየህ ብትውል ምን ያክል ሰይጣን እንደምትሆን አስበው… በጠዋት ተነሥተህ ፌስቡክህን ከፍተህ «እስቲ ኦርቶዶክሱ አክቲቪስት እገሌ የጻፈውን ጽሑፍ ላንብብለት… 👇
8/ «...በዚያውም ፕሮቴስታንቱ እገሌ እና ሙስሊሙ አክቲቪስት እገሌ የጻፈውን ላንብብ… ከዚያ ኦርቶዶክሱ እገሌ ፋርማሲ ገብቼ መድኃኒት እገዛና ስመለስ በሙስሊሙ እገሌ ቤት በኩል አልፌ ወደሥራ እሄዳለሁ።...»👇
9/ «...ከዚያ መሥሪያ ቤት ሄጄ ፕሮቴስታንቱ አለቃዬ የሚሰጠኝን ሥራ እሠራለሁ። ማታ ጊዜ ከተረፈኝ ኦርቶዶክሱ ባለሃብት ያሠሩት ሆስፒታል ሄጄ የታመመ ዘመዴን እጠይቃለሁ። መንገድ ላይ ላገኘሁት ኦርቶዶክሳዊ የኔቢጤ ምጽዋት እሰጣለሁ።...»👇
10/ «...ከዚያ ቤት ገብቼ በኦርቶዶክስ ዜና አንባቢ የሚነበበውን ዜና አዳምጬ ከፕሮቴስታንት ነጋዴ ሱቅ በገዛሁት አንሶላ ላይ እተኛለሁ።…»

ከምር እንዲህ የሚያስብ ሰው አዕምሮው የነተበ ብቻ ነው። በራሱ አስተሳሰብ ሊያፍርም ይገባል። 👇
11/ እንደሙስሊምነቴ ብዙ የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ብዙ በደል አድርሰውብናል። አንድም ቀን ግን «ኦርቶዶክሱ ባለሥልጣን እገሌ እንዲህ አደረገን»፣ «ፕሬቴስታንቱ ባለሥልጣን እገሌ እንዲህ አደረገን» የሚል ዘመቻ አድርገን አናውቅም። 👇
12/ የሰዎች ምግባር እንጂ ሃይማኖታቸው ታይቶን አያውቅም። እንዲያ ቢታየን ነውር ይሆን ነበር።

እንደግሌም ቢሆን ብዙ አክቲቪስቶች እና ጋዜጠኞችን ስከታተል እውላለሁ። ሃይማኖታቸው ግን አይታየኝም። 👇
13/ ሲሣይ አጌና ወይም ደረጄ ሃብተወልድ ስህተት ቢናገር «ኦርቶዶክሱ ደረጄ እንዲህ እንዲህ ተናገረ» ብዬ አላስብም። ደረጄ እንጂ «ኦርቶዶክሱ ደረጄ» አይደለም የሚታየኝ። ብዙ ፕሮቴስታንት አክቲቪስቶችን አነባለሁ። በሃይማኖት ግን አልተረጉመውም። 👇
14/ ምክንያቱም ነውር ነው። እንዲህ ዓይነት መነጽር ለብሶ መኖር ዕኩይነት ነው። እንደኢትዮጵያ ባለች ብዝኃ ሃይማኖት አገር ውስጥ ይህንን ማድረግ ብዙ አደጋ አለው። ለጊዜያዊ፣ ፖለቲካዊና ፕሮፓጋንዳዊ ጥቅምን እንዲህ እያደረጉ ያሉ ሊያፍሩ ይገባል!👇
15/ የሚያሳዝነው ደሞ ይህን ክፉ መነጽር ለብሰው የሚዞሩት «ኢትዮጵያኒስት» እና «የአንድነት አቀንቃኝ» እንደሆኑ የሚፎክሩ ሰዎች መሆናቸው ነው። ገና ለገና የኦሮሞ ብሄርተኞችን ለማሳጣት በሚል አገሪቷ ላይ የሚቆፍሩት ጉድጓድ ጥልቀት አይታያቸውም።👇
16/ «እንወዳታለን እንዋደቅላታለን» የሚሏትን ኢትዮጵያ የመተሳሰሪያ ገመዶች ሁሉ ለመበጣጠስ ይሞክራሉ። የሚሠሩት ነውር አይታወቃቸውም። ያሳዝናል! 😭 [ Thread Ends Here]

#ነውር #ነውረኛመነጽር #ዕኩይነት #ፌክኢትዮጵያኒስት #ፌክአንድነት
Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh.

Keep Current with Isaac Eshetu

Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

Twitter may remove this content at anytime, convert it as a PDF, save and print for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video

1) Follow Thread Reader App on Twitter so you can easily mention us!

2) Go to a Twitter thread (series of Tweets by the same owner) and mention us with a keyword "unroll" @threadreaderapp unroll

You can practice here first or read more on our help page!

Follow Us on Twitter!

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3.00/month or $30.00/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!