ህብረ ትርኢት Profile picture
Sep 17, 2020 26 tweets 6 min read Read on X
ሐሙስ የቀን ቅዱስ
💚💛❤

ሳምንታዊ የአይሬ ፕሮግራማችንን ይዘን ቀርበናል❤

ገባ ገባ ቦታ ቦታችሁን ያዙልን🙏
#ReadZinetMuhaba
🎹🥁🎼🎧🎤🎷🎺🎻🎸
ቤተሰቦች ዛሬ በሳምንተዊው አይሬ መሰናዶአችን ስለ አንጋፋዋ እና ተወዳጇ ዚነት ሙሃባ ጥቂት ልናካፍላችሁ ወደናል።
በ1959 ዓ/ም ደሴ ቁርቁር በተሰኘች አካባቢ ከሸህ ሙሃባ ይመርና ወ/ሮ ይመኑ ሙላት ቤት ደስታ ሆነ። ሴት ልጅ ይፈልጉ ለነበሩት እመት ይመኑ ባሰሙት ፀሉት ባደረሱት ስለት ከ12 ወንድ ልጆች በኋላ 13ኛ ልጃቸው ተወለደች።
ኋላ ከ1970ዎቹ መጨረሻ እስከ 80ዎቹ መጀመሪ በሙዚቃዋ ኮከብ ሆና ልታበራ ዘኒት ሙሃባ ተወለደች። ImageImage
ማንጎራጎርን ገና በማህፀን ሳለች ከእናቷ የወረሰችው ዘኒት በአፍላ እድሜዋ ቀጠለችበት። የቤት ስራዋን ስትሰራ፣ ተልካም በየመንገዱ ማንጎራጎር የዘኒት መለያዋ ሆነ።
በአንዱ ደገኛ ቀን ደሴ ፒያሳ ላይ ቀይ መብራት አካባቢ ባለ አንድ ሆቴል የቦረና ሙዚቃ ስትጫወት በሰሙ የባህል አምባ ሰዎች አይን ላይ አረፈች። በዛች ቀን በድምፇ የተማረኩት የባህል አምባው መለማዮች የላሊበላ የባህል ቡድንን እንድቀላቀል ጠሯት።
የልጅንት ህልሟ ነበርና አላንገራገረችም። በተዛዋዣነት የባህል ቡድኑ አባለ ሆነች። የመጀመሪያ ስራዋንም በወቅቱ ይከበር በነበረው የአብዮት በዓል ቀን በአደባባይ አቀረበች።
ቀድሞም ጥሪዋ ለዘፋኝነት ነበርና በዚሁ የባህል ቡድን አዘጋጅነት
ይቀርብ የነበረው ሳምንታዊው የዝክረ ኪነጥበብ ፕሮግራም ላይ ታቀነቅን ጀመር።

ዘመን አይሽሬዎቹን አነ"ከምበል ደፋ"ን በዚህ መድረክ በማቅረብ ነገሰች። በድምፇ የተማረኩ ደግመው ደጋግመው "ቢስ ቢስ" አሉ።
እንደው ከምበልን ጨምሮ ስምንት አዳዲስ ስራዎቿን በዚህ መድረክ ለታዳሚያን ስታቀርብ ቆየች።
"እንደው ከንበል"

እንደው ከንበል እንደው ዘመም
እንደው ከንበል ይላል ጎፈሬው
ወጥቶ እስኪመለስ ልቤማ አያምነው x2
መንገደኛው ልቤ መንገደኛ ወዶ
ከማያቀው ሃገር ተሻገረ ማዶ አይ ማዶ
ቀንም ስራ አልሰራ እረፍት የለኝ ማታ አይ ማታ
ከሆዴ ተቋጥሮ የሩቅ ሰው ትዝታ ትዝታ
ሃሳብ ሳጠነጥን ስቋጥር ስፈታ ስፈታ

ሙሉ ሊንክ❤
የሙዚቃው አዘጋጅ ዳምጤ መኮንን የስራዎቹን መወደድ ሲረዳ ከስምንቱ ሙዚቃዎች ላይ ሌሎች ኹለት አዲስ ሙዚቃዎችን በመጨመር በማራቶን ሙዚቃ ቤት በኩል እንዲታተም ተደረግ። ይሄም የመጀመሪያዋ ካሴት ሆነ።
ሙዚቀኛውን በማበረታታት የሚታወቁት የማራቶን ሙዚቃ ባለቤት አቶ ታምሬ ውል ያሰፈረሙበትን ክፍያ በእጥፍ አሳድገው ለግጥም ለዜማ እና ለድምፅ ለአያንዳንዱ በወቅቱ 3000 ብር እንደከፈሉ ይነገራል።
የዚነት ሙዚቃዎች ምንጩ ያደገችበት ወሎ ግጥሞቹም ፍቅር ከሚቀምስበት የእረኛው መስክና የጉብሏ ውሃ ምንጭ ነው። ለዛዋ አድማጯን ማረከ። በየቦታው ዚነት ነገሰች። የ9ብሩ ካሴት 60ብር እስኪሸጥ ደረሰ።
"የአርሶ አደር ልጅ ነኝ"
እቴ ምላስ ጉልበቱ
አትፎግሪኝ በጠዋቱ
የአርሶ አደር ልጅ ነኝ የደገኛ የደገኛ x2
በስንዴ ለውጪኝ ካንቺው ማኛ ካንቺው ማኛ
አንቺ ቆለኛ x2
የማነህ ብልጣብልጥ ቆዳህ ሞኝ መሳይ x2
ምነወ መቸኮልክ ከወቀጣው ላይ
ቅድሚያ በገበያው ተስማምተናል ወይ
ቆለና ደገኛ መባባሉን ትተን
ያለሽን ያለኝን ባንድ ላይ አስማምተን
ነጩን ጤፍ እንጀራ ስንዴውን ዳቦ አርገን
ብንበላ ይሻላል ባንድ ላይ ተስማምተን

ሙሉ ሊንክ❤
ልጅነቷን ለቀረፀች ማንነቷን ላበጀች ሙዚቃ ራሷን ሰጠች። አልበጀም። ለሙዚቃ ያላት ፍቅር እና ትዳሯ እዚህና እዛ ተፋጠጡ። ልታስታርቅ ብትጥርም አልተሳካም። አደላች። መረጠች። ተረታች። ለሙዚቃ።
ከዚህ በኋላ ኮከብ ሆና የወጣችበት የወሎ ላሊበላ የባህል ቡድን በተለያየ ምክንያት ተዳከመ። ዚነትም በፅኑ ታመመች። የሁለተኛ አልበሟን ህዝብ እንዴት እንደተቀበለው ሳትሰማ አለፈች። አረፈች። ሳትጠገብ ተለየች።
ስንብትህ ይመር ትለናለች እንግዲ በዚያ ተስረቅራቂ ድምጿ

እንኳን ሆንኩህ እንጂ ካሰብክለት ማደር
መሄዱን ስታስብ መብት የለኝ አላስቀር x2
ባይሆን ግፉን ፈርተህ ስንብትህ ይመር
ስንብትህ ይመር
በውድ ሃገር ፍቅር ዋጋ አለው
ጣል ጣል ናቅ ናቅ ሳታረገው
አሰር ጠበቅ አርገህ ሳታረክሰው
ሚዛኑ ሚስጥር ነው አትሸንሽነው
ወይ ወረት ወይ ወረት
አይ ወረት x2

ሙሉውን ለምትሹ❤
ዚነት ሙሃባ በሰጠችን ጥቂት ግን ደግሞ ጣፋጭ ሙዚቃዎች ሁሌም አብራን ትኖራለች።
የኔ ናፍቆት የተሰኘውን ውብ መዚቃ ደግሞ በመቀጠል ተጋበዙልን😍

የኔ ናፍቆት ፍቅሬ ነህ ህይወቴ
ባንተ መውደድ ሳስቷል ሰውነቴ
መውደድ ፍቅር ብቅ በል በሞቴ
ፍቅሬ እባክህ ናልኝ
መውደድ ናፍቆትህ ጎዳኝ
እኔስ መሞቴ ነው ብትመጣልኝ ምነው
ያንተስ የብቻው ነው
ጋራ ሸንተረሩን ዞረህ ልቤን ሰንጥቀህ የሄድከው
በውበትህ አማለህ ወለላ የኔ ህይወት አንተ የሩቅ ሰው
ልቃኝህ በሃሳቤ በትዝታህ

ሙሉ ሊንክ👇
አንተ ልጅ ናልኝ በተሰኘው ውብ ሙዚቃዋ የዛሬው አይሬ ፕሮግራም እንቋጫለን።

አንተ ልጅ ናልኝ አንተ ልጅ ናልኝ
ፍቅሬ እባክህ ናልኝ
የልቤ የልቤ
ከቶ በምን ቋንቋ ልግለፀው መውደዴን
እባካችሁ ሰዎች እባካችሁ
ያንን ልጅ አማልዱኝ ለፍቅር ብላችሁ
እባካችሁ
ያንን ልጅ አማልዱኝ ዘመድ ወዳጆቹ
አድራሻውን ስጡኝ የቅርብ ጓደኞቹ

መሉውን ሊንክ ለምትሹ👇
ምንጮቻችን አማራ ማስ ሚዲያ ሸገር ራዲዮ ስንክሳር ፕሮግራም እና ዮቲዮብ ናቸው። 🙏
ቤተሰብ ያልሆናችሁ ተቀላቀሉን @Chobe2020 ለወዳጅ ዘመድም አዳርሱ።

አብራቹን ስለቆያቹ እናመሰግናለን።
ብሩህ ምሽት።
💃💃💚💛❤

• • •

Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh
 

Keep Current with ህብረ ትርኢት

ህብረ ትርኢት Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

PDF

Twitter may remove this content at anytime! Save it as PDF for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video
  1. Follow @ThreadReaderApp to mention us!

  2. From a Twitter thread mention us with a keyword "unroll"
@threadreaderapp unroll

Practice here first or read more on our help page!

More from @Chobe2020

Oct 18, 2020
እንደምን ውላችኋል ቤተሰብ? ሁሉ ሰላም? ሁሉ ተማም?
እስኪ እባካችሁ አማክሩን ❣️

A Thread
ጊዜ ወስዳቹ አንድታነቡት ከአክብሮት ጋር እንጠይቃለን
ትላንት የቅዳሜ የሙዚቃ ምርጫ ፕሮግራማችንን ሳንሰራ ስለቀረን በጣም ከፍቶን ነበር። ወዳጆቻችን ተደስተው በናፍቆት እንደሚጠብቁን ሁሉ አልፎ አልፎ ከቅጂ መብት (copy right) ጋር በተገናኘ “ይሄ ነገር ልክ ስራ ነው?” የሚሉም አስተያየቶች ይደርሱናል።
@Chobe2020 በፍፁም ህግን በሚፃረር መልኩ ምንም አይነት ስራ የመስራት ፍላጎቱ የለንም ጥያቄዎቹንም ሆነ ተግሳጾቱን በሙሉ ልብ እንቀበላለን።
Read 17 tweets
Oct 17, 2020
አበሩስ እንዴት አደራችሁ😍

ከሰሞኑ የተለቀቀውን የ ጠረፍ/Terry Teref ሙዚቃ ስራ ስሙትማ 💖

Terry የምትታወቀው በአንጋፋ ድምፃውያን የተሰሩ የሚጣፍጡ የድሮ የፍቅር ዘፈኖችን በራሷ ዘይቤ በመስራት ነው።

መልካም ቅዳሜ ለሁላችሁም
A thread ....
ሀገሬ ኢትዮጵያ ለምለሟ አበባዬ
ሳስብሽ ይፈሳል እምባዬ በላዬ
ሰላም ላንቺ ይሁን ለውዲቷ እናቴ
ካለሁበት ቦታ ከልብ ከናፍቆቴ
ይሄም ሀገር ሀገር ሀገር ይላል ሀገር ይሄ ሀገረ ብርቁ
አህም እኔም ሀገር ሀገር አለኝ ሀገር የሚታይ በሩቁ
(የአስቴር አወቀ)
ኦሆሆይ የአይኔ አበባ ነህ የምወድህ
ኦሆሆይ ዘወትር ከልቤ የማረሳህ
ኦሆሆይ አይኖቼ ከአይኖችህ አልነቀል አሉ
ኦሆሆይ መውደድ ያስገምታል ሰዎች አንድ በሉ
ተጋባብኝ ግራ ምንድን ተሻለኝ
ፍቅርዬ የአይኔ አበባ ለምን ሸሸኸኝ
(ነዋይ ደበበ)
Read 9 tweets
Oct 15, 2020
ሐሙስ የቀን ቅዱስ
💚🧡❤️
ሳምንታዊ የአይሬ ፕሮግራማችንን ይዘን ቀርበናል
💚🧡❤️

ገባ ገባ በሉ ቦታ ቦታችሁን ያዙልን
🙏

#ReadMeryArmde

🥁🎹🎸🎺🎷🎹🎼🎶🎚️
በክራር ጨዋታዋ እና በወፍራም ድምጿ በማንጎራጎር የምትታወቀው አንጋፋዋ አርቲስት ሜሪ አርምዴ የዛሬው የአይሬ ዝግጅታችን ትኩረት ናት።

በ1915 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ዶሮ ማነቂያ ከሚባለው ሰፈር ነው የተወለደችው።
ለሙዚቃ ገና በጠዋቱ መጠራቷን ስታብራራ "በሠፈራችን መደዳውን ጠጅ ቤት ነበር።ዘውትር ይዘፈናል። እኔም የታዘዝኩትን ትቼ ወደዚያው ሄጄ ቀስ ብየ እያሾለኩ በመጋረጃ ውስጥ እመለከታለሁ።የዚያን ጊዜ ዘፋኞቹ እነ ባፈና ወልዱ፥ ንጋቷ ከልካይ፥
Read 18 tweets
Sep 27, 2020
ወዳጆች ይህንን የጥላሁን ገሠሠ "አምሳሉ" የተሰኘ ሙዚቃ ስራ ታውቁ ኖርዋል?

አንዲት ወዳጃችን ስሜ ይቆይ ብላ ይህንን ድንቅ ሙዚቃ አቀብላናለች። እግዜር ይክብርልን ብለናል።

ለኛም ይሄ የመጨረሻው ሙዚቃችን ይሆናል ለዛሬ

ግጥሙን ልብ በሉ 💚💛❤️
አበባው ለምለሙ ዛፉ ሳሩ ቅጠሉ
በፍጥረት አለም ላይ አምሮ የሚታይ ሁሉ
ውብ የሆነው ነገር የሚያምረው በሙሉ
ሀሩ ቀጭን ኩታው ለጌጥ እንቁና ሉሉ

የወርቅ የአልማዝ መስቀሉ እና ጥርባን ስራው በሙሉ
ጨዋነት ደግነቱ እና ቁም ነገሩ በሙሉ
ምንም ነገር ሳይቀረው መልኩ ያንቺ እኮ ነው አምሳሉ
Read 7 tweets
Sep 27, 2020
"በባይተዋር ጎጆ" ደግሞ ከጥላሁን ገሠሠ በጣም ከሚደነቅለት የፍቅር ዘፈኖቹ ውስጥ ደግሞ።

እያንዳንዱ ስንኝ ያዘለው ተማፅኖ ናፍቆት ስስት እና ፍቅር አጃይብ ያስብላል ❣️❣️❣️
በባይተዋር ጎጆ በባይተዋር አልጋ
እንግዲህ ለሊቱ ዋ እንዴት ይንጋ

ያረፈብሽ ክንዴ አሀ ያለበስኩሽ ኩታ
ያደርንበት ጎጆ አሀ ያሞቀን መኝታ
ሀቄን ይግለፅልሽ አሀ የፍቅሬን ሁኔታ
የኔ አካል እባክሽ እባክሽ
የኔ አካል እባክሽ በሞቴ
አልቋል ሰውነቴ በሞቴ
Read 6 tweets
Sep 27, 2020
መልካም ልደት ለሙዚቃው ንጉስ ጥላሁን ገሠሠ ❤️
ድንቅ ስራዎቹን ትቶልን አልፉዋል ፤ እግዚያብሔር ነፍሱን በገነት ያኑራት እያልን ፤ "የዘንባባ ማር ነሽ" የተሰኘውን ሙዚቃውን እንጋብዛቹ 😍
የዘንበበ ማር ነሽ እም ወለላሽ የረጋ
አልደርስብሽ አልኩኝ አሀ እጄን ብዘረጋ
የዘንባባ ማር ነው ፍቅርሽ
ቄጤማን ይመስላል ጸጉርሽ
ምርኩዜ ወደቀ በትሬ
አይን አይንሽን ሳይ ተገትሬ

ባንቺ ለዛ ሁሉም ያድራሉ ሲያልሙሽ
የዘንባባ ማር ነሽ
አዎ
የዘንባባ ማር ነሽ ንቦች የቀስሙሽ
በጣም ቀዝቀዝ ያለ ውርጭ ነው ሰፈሬ
የቀጩን መድሐኒት
አዎን
የቀጩን መድሐኒት ስጪኝ ለከንፈሬ
Read 6 tweets

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3/month or $30/year) and get exclusive features!

Become Premium

Don't want to be a Premium member but still want to support us?

Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal

Or Donate anonymously using crypto!

Ethereum

0xfe58350B80634f60Fa6Dc149a72b4DFbc17D341E copy

Bitcoin

3ATGMxNzCUFzxpMCHL5sWSt4DVtS8UqXpi copy

Thank you for your support!

Follow Us!

:(