Thread 1
ኢትዮጵያ ነገ:-
ለብዙዎቻችንን ድንገቴ በሆነ ሁኔታ የዛሬ ሶስት ሳምንት ሀገራችን ኢትዮጵያ በግትርና በማን አለብኝ መሪዎቿ (በሁለቱም ወገን) የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቃለች። እንደ እኔ እምነት ይህ ጦርነት እንዳይሆን ማደረግ..
Thread 2
የሚቻልባቸው በርካታ መንገዶችና ያመለጡ እድሎች ነበሩ። ይሁንና ስለፈሰሰ ውሀ መብስልሰሉን ትተን ነገ በምን ሁኔታ ሀገራችንን መታደግ እንደምንችል መነጋገር ብንጀምር አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ።
Thread 3
የጦርነት ዋጋ:-
በአለም ላይ በተደረጉ ሁሉም ጦርነቶች እንደታየው መጀመርያም መጨረሻም ላይ በአካል በምጣኔሀብት በስነልቦና የሚጎዳ ሰላማዊ ህዝብ እንጂ ተፋላሚ ጦር አንጋቾች አይደሉም። በተለይ በዚህ ጦርነት ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ..
Thread 4
የተጎዳው ጦርነቱ የተደረገበት የሀገራችን ክፍል የትግራይ ህዝብ ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም አውድማነት ይታወቅ የነበረው ከሌላው የሀገራችን ክፍል ይልቅ ማንም ሰው የማንም ብሄር አባል ቢሆን ያለስጋት ወጥቶ ይገባበት የነበረው ትግራይ
Thread 5
በሶስት ሳምንት ውስጥ በተከፈተበት ጦርነት ከ50ሺ በላይ የሚሆነው ቀዬውን ለቆ ተሰዷል። ገና ቁጥሩ ያልታወቀ ሰላማዊ ሰው ተገድሏል። ንብረቱ ወድሟል። ከተሞቹ በቦምብ ተመተዋል። በቀላሉ የማይሽር የስነልቦና ስብራት ደርሶበታል።
Thread 6
ከጦርነቱ በሁዋላ:-
ከላይ ያየነው የጦርነቱን ዋጋ ሲሆን ፣ እስቲ መቼም ጦርነቶች አሸናፊና ተሸናፊ ይኖራቸዋልና ከዚያ በሁዋላ ምን ሊሆን ይችላል? በዚህ ጦርነት ያለውን ሀይል ሁሉ አጠራቅሞ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ተቋም ጥሪት አሰባስቦ..
Thread 7
የዘመተው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እንዳሰበው ተሳክቶለት የክልሉን መናገሻ መቀሌን ቢቆጣጠር ጦርነቱ ያበቃል ማለት ነው? እኔ አይመስለኝም። ምክንያቱም ህወሓት በአላማው አሳምኖ ያሰለፋቸው ብቻ ሳይሆኑ የክልላቸው መወረር በግዴታ..
Thread 8
(አንዳንድ የመንግስት ደጋፊዎች እንደሚፎልሉት) መገበር የሚያስቆጫቸውና በማንነታቸው ፣ በስማቸው ምክንያት የተጠቁ ይህንንም እንደውርደት የሚቆጥሩት ትግራዎትን ይዞ በሽምቅ ውጊያ (Insurgency) እንዲሚቀጥል አምናለሁ። Image
Thread 9
ይህ ደሞ ሀገራችንን ለተራዘመ የግጭት ረመጥ ውስጥ የሚከታት ነው። በተለይ አሁን በስፋት እንደሚታየው ተጋሩን ማሳደዱ በማንነታቸው ምክንያት ማጥቃቱ ማዋረዱ ንብረታቸውን መንጠቁ ማግለሉ ከቀጠለ ዜጎችን ወደ ህወሓት መግፋትና በሰውና ቂሳዊ..
Thread 10
..ሀይል ማጠናከር ነው የሚሆነው። በተለይ መንግስት በትግራይ ላይ ከህዝቡ ፈቃድ ውጪ አዛዥና ናዛዦችን መሾም ካመጣ (አሁን በቅርቡ እንዳደረገው) እጀግ ጉልበታም በመጨረሻም መውደቂያውን የሚያፈጥነለት ጠላት ለራሱ እንደሚፈጥር ይወቀው። Image
Thread 11
ይቅርታ:-
መንግስት ሰበብ የሌለበት ፍፁም ልባዊ ይቅርታ የትግራይን ህዝብ መጠየቅ አለበት። (No if, no but) ሰላሙን አደፍርሷልና ፣ ህይወቱን አጥፍቷልና ፣ ከተሞቹን አውድሟልና ብዙ ሺዎችን እንዲሰደዱ አድርጓልና ምክንያት ያልደረደረ ይቅርታ
Thread 12
የመጠየቅ ግዴታ አለበት። "..ህወሓትም ለዚህ ተጠያቂ ነው። እሱስ?.." ለሚሉ ፣ መንግስት የህወሓትን አመራር ይዤ ለፍርድ አቀርባላሁ ስላለ ይዞ ካቀረባቸው 'ፍርድ ቤት' ይጠይቃቸው እንጂ የፖለቲካ ድርጅት ላጠፋው ህዝብ ዋጋ መክፈል የለበትም።..
Thread 13
ካሳ :-
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ፍጹም ባላስበው መንገድ ባልጠበቀው ጊዜ የትግራይ ህዝብ በተከፈተበት ጦርነት ሰላማዊ ህይወቱን ብቻ ሳይሆን ፣ንብረቱን ከነጋዴ እስከ ገበሬ አጥቶ ከፍተኛ አካላዊ አእምሮዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።
Thread 14
ስለሆነም መንግስት በተለይ በዚህ ጦርነት የህይወት የአካል የቁስ ጉዳት ለደረሰባቸው አስተማማኝ ካሳ የመክፈል ግዴታ አለበት። በዚህ መልኩ የአካባቢውን ሰላም መንግስት ለማረጋጋት መሞከር ይችላል።
Thread 15
ህጋዊነት :-
መሬትን በሚመለከት በተለይ የአማራን ወጣት "ትግራይ ሄደህ መሬት ንጠቅ" በሚል አይነት ፕሮፓጋንዳ አንሳስተው በዘር በቋንቋ በሀይማኖት በስነልቦና አንድ የሆነን ህዝብ ደም ያቃቡትን የብአዴን ወንጀለኞች መንግስት አደብ ማስገዛት
Thread 16
..አለበት። በአንድ ሀገር የሚገኝ አስተዳደራዊ ክልል የሚካለለው በህግ በተቋቋመ ተቋም እንጂ በታጣቂዎች አፈታሪክ ላይ ተመስርቶ በተሰመረ ካርታ አይደለም። መንግስት በዚህ ጉዳይ የህዝበኝነት (populist) አካሄዱን እርግፍ አርጎ ትቶ ..
Thread 17
የፈረጠመ ህግን የማሰከበር ሀላፊነት አለበት።
በትግራይ ላይ በጦር አውሮፕላኖች በከባድ መሳርያ በብዙ ሺ ወታድሮች በድሮን "ህግ አስከብራለሁ" ካለ ሌሎች አካባቢዎች ግን ህግን ሲጥሱ የማሽኮርመም ባህርይው ፀረ ትግራይ ያሰኛዋል።
Thread 18
የልሒቃን እና የባለሀብቶች መብት:-
መንግስት በአሁኑ ወቅት እያደረገ ያለው እጅግ አጸያፊ አሳፋሪ የሆነ የትግራይን ልሒቃንና ባለሀብቶች የማዋከብ የማሳደድ የመዝረፍ ነጥሎ የማጥቃት ባህርይ ባስቸኳይ መቆም አለበት። የትግራይን ህዝብ ልብ..
Thread 19
ለማለዘብ እንጥፍጣፊ ተስፋ እንኳ ካለው በነዚህ ልሒቃንና ባለሀብቶች ነው ሊሆን የሚችለው። እወቀታቸው በህዝባቸው መካከል ያላቸው ተቀባይነት ዋጋ ያለው (asset) ነው እንጂ ኪሳራ (liability) አይደለም። አምርረው ቢቃወሙት እንኳ ትንሽ እንኳን
Thread 20
ቅቡልነት ለማግኘት ከመታገስና ከማዳመጥ ይልቅ ማሳደድ ማጥመድና ማንገላታት ፣ በሌላ በኩል አድርባይና እበላ ባዮችን ማስጠጋትና ከእነሱ ጋር መሞዳሞድ ዋጋ ቢስና ውድቀትን ማፋጠኛ መሆኑን መረዳት አለበት።
Thread 21
በአሁኑ ወቅት በውጭ ያሉ ትግራዎት በጦርነት ቀጣና ውስጥ ያሉ ቤተሰብ ወዳጆቻቸው እጣ ፈንታ በእጅጉ አሳስቧቸዋል። ለዚህም ነው ጠዋት ማታ አለም አቀፍ ድርጀቶችን የመገናኛ መንገዶች እንዲከፈቱ እየተማጸኑ ያሉት። እኔም ከነሱ ጋ አብሬ..
Thread 22
ድምጼን አሰማለሁ። መንግስት ጦርነቱን እያሸነፍኩኝ ነው ብሎ ካመነ ፣ ቢያንስ እነዚህ ዜጎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሊገናኙ የሚችሉበት የስልክ መስመር ሊክፍትላቸው ይገባል። በዚህ ሁኔታ እጅግ አነስተኛ በሆነ መልኩ እንኳን ቢሆን መልካም..
Thread 23
..ጎን እንዳለው (ካለው) ማሳየት ይችላል። ያለበለዚያ ግን የብዙዎች እምነት የሆነውን መንግስት ጸረ ትግራይ ነው የሚለውን አመለካከት ያጠናክረዋል።
Thread 24
ይህንን የቀጣጠልኩት የሀገራችን የወደፊት ሁኔታ እንቅልፍ ስለሚነሳኝ ይመጥናል ካልኳቸው መውጫ መንገዶች ጥቂቱን ልተንፍስ ብዬ ነው። እንደጦርነቱ አካሄድ በሚቀጥለው ሳምንት በተመሳሳይ ርእስ እመለሰላሁ። አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ።

• • •

Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh
 

Keep Current with Naty Yifru (ናቲ ይፍሩ)

Naty Yifru (ናቲ ይፍሩ) Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

PDF

Twitter may remove this content at anytime! Save it as PDF for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video
  1. Follow @ThreadReaderApp to mention us!

  2. From a Twitter thread mention us with a keyword "unroll"
@threadreaderapp unroll

Practice here first or read more on our help page!

More from @Natberh

8 Nov
Thread 1
ይህ ቅጥልጥል በአሳዛኝ ሁኔታ የኢትዮጵያ የስልጣኔ መሰረት የሆኑትን ሰሜን ኢትዮጵያውያንን አፋጅቶ ለማዳከም በ "ብልጽግና ወንጌል" ፖለቲካዊ የሀይማኖት ርእዮተ ዓለም በ @AbiyAhmedAli ጦርነት ሰለታወጀበት የኢትዮጵያ ክፍል #ትግራይ ነው Image
Thread 2
እኛ ኢትዮጵያዊያን የ3ሺ ዘመን ታሪክ አለን ብለን የምንመጻደቅበት አክሱም ፣ የኢትዮጵያ ስርወ መንግስት አሰራር (State Craft) እና የስልጣን ተዋረድ (Hierarchy) ጥንስሱ የተጀመረበት የማንነታችን መነሻ ያለው አክሱም ትግራይ ነው። Image
Thread 3
ከአውሮፓውያን ቀድማ ከአብርሀማዊ እምነቶች አንዱ የሆነውን ክርስትናን የተቀበለችው ኢትዮጵያ ለመሆኗ የምትመስክር በኢትዮጵያ ተዋሕዶ አማኞች እንደሚታመነው አምላክ ለሙሴ የስጠው የአስርቱ ትእዛዛት ጽላት ያረፈበት አክሱም ትግራይ ነው። ImageImage
Read 20 tweets

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3/month or $30/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!

Follow Us on Twitter!