ወልቃይትና ራያ
==========
አፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ መውደቃቸውን ተከትሎ አፄ ዩሀንስ በንጉስነት ተሾሙ። ታዲያ አገዛዛቸው ሀይል ነበረበትና አገዛዛቸውን በአደብና በወጉ እንዲያደርጉት መካሪ ከወሎ ምድር በቅለው ነበር በጊዜው።
"ዓባይ በጣና ላይ መሄዱ ለምን ነው?
ትንሹ ሲያጠፋ ትልቁ ሊችል ነው፣
ቢያከፋም ቢያበጅም ዓባይ ማለፉ ነው
ሰውን በግዴታ የሚገዛው ማነው?
ከምክር በስተቀር የቀረው ከንቱ ነው"
"አንተም እድሜህ አጭር ወይ ዘርህ አይገዛ
ጎርፍ ደርሶ አይወስድም አለቅጥ ካልበዛ
እንጨት ከደረቀ ቢቀቡት አይወዛ
ሐበሻ ክፉ ነው አይምሰልህ ዋዛ
መተማ እስቲጠራህ በብልሃት ግዛ"

ብለው ምክረውት ነበር።
እመክርህ ነበረ መች እሺ ትላለህ
ሀሳብህ ብዙ ነው መንገድ ታበዛለህ
መተማ ለመዝመት አሁን ትሄዳለህ
መመልስክን እንጃ እዛው ትቀራለህ
በድርቡሽ ጎራዴ ራስህን ታጣለህ::
አንድ ዓመት ሲቀረው ምኒልክ ሊነግሥ
አላህ መተማ ላይ ይስላል መቀስ
በደም አጨማልቃ የምትቆራርስ
እራስ የምትቆርጥ ያውም የንጉሥ
አንደዜ ተመታች የማታላውስ

ይሄ ሁሉ ለንጉሱ ተነግሯቸው ነበር ። አልሰሙም።
አራት ወር ሲቀረው ምኒልክ ሊነግሥ
በመተማ በኩል ትጨሳለች ጭስ
ጭሷ በራስ ገብታ የምታስነጥስ
እጅግም አትበጀው ለአጼ ዮሐንስ
አላህ ሽቶበታል አንገቱን ሊቀምስ

ንጉሱ ጭካኔያቸውን ትተው ሀበሻን በብልሀት እንዲመሩ ቢመከሩ አልሰሙም።
ምክሩን ከመስማት ይልቅ መካሪውን ማንቋሸሽ ቀጠሉ።

እናም እንዲህ ተባለ

እውቀትም የላቸው አሉን ጥንብ እርኩስ
ብለው ሰደቡን ደብተራና ቄስ
ሄጄ ልናገረው ለአጼ ዮሐንስ
ፈርጀለት ነበር መቅደላ ሲፈርስ
እንዴት የነቢ አሽከር ይሆናል እርኩስ?
የሰማም ያልሰማም ያልቅስ
መች እኔ እፈራለሁ ደብተራና ቄስ
መተማን ድል አድርጎ እሱ ቢመለስ
እንግዲህ የኔ ጫት ጥንብ ናት እርኩስ
መተማ ካልሄደ እኔም ጫት አልቀምስ

ንጉሱም ጦራቸውን ጭነው ወደ መተማ ዘለቁ
ጦሩን አስከትሎ መተማ ሲደርስ
ከበቅሎው ወረደ አጼ ዮሐንስ
የጦሩን መከታ ጋሻውን ሊለብስ
እሱ እራሱን አጥቶ ሰውን ሊያስጨርስ
በጥረት አይድንም ጥፋ ያለው ነፍስ

አሁን ያለውን የወልቃይትና የራያን ነገር እዚህ ላይ አስቡት
እንዴት በገዛ እጁ ሞት ይመኛል ሰው?
መተማ አትሂድ ብዬ ብመክረው
መቸ ይመለሳል ያዘዘበት ሰው
ደም እየሸተተው ሞት እየጠራው
እንዴት ሰው ለአንገቱ አያዝንም ወይ ሰው?

የህይወት እጣ ፋንታ መተማ ቡላዋን ስላ ንጉሱን ጠበቀች።
የአህያ ልጅ በቅሎ በብር ተሸልማ
ዮሐንስን ይዛ ወረደች መተማ
ከጌታዋ ራስ ጋር በቁም ልትቀማ
ስንቱን ሰው ፈረጀው ደጉ አገር መተማ
ስንቱን አርዶት ነበር እስላም እንዳይለማ
ምኒልክ ደስ አለው ምጡን ሲፈረጅ
እኔም ጫት በመቃም ነጀ ወጣሁ እንጅ
እስላምን የሚወድ ወደፊት ይምጣ እንጅ
ዮሐንስ ክፉ ነው የለውም ወዳጅ
መተማ ደጉ አገር ገላገለን እንጅ

የወሎው የቦሩ ሜዳ ጭፍ ፋ እዚህ ላይ ነው የሚጠቀሰው።
አላህ ገላገለን በዟሂር መከራ
እንግዲህ ምኒልክ አይዞህ እንዳትፈራ
ዮሐንስ ሊሄድ ነው ጦሩን እየመራ
ማረድ የለመደ መቼም ሞት አይፈራ
ሞቱ ብላሽ ሆነ እንዲህ ሲንጠራራ
አንተም ጨካኝ ነበርክ ጨካኝ ወረደብህ
እንደ ፍሪዳ ላም በቁምህ አረዱህ
በቅሎና ገጧ ጋር በቁሟ ማረኩህ
እራስክን ቋንጣ አርገው ሥዕል አደረጉህ
አላፊው አግዳሚው እንዲሰደድብህ
አሁን በትግራይና በፌደራል መንግስት ዙሪያ የታየው ለመተንተን ያስቸግር የነበረው የጦርነት ፍጥጫ ምንም እንኳ በመከላከያ ሰራዊት የዘመቻ ድል ያለቀ የመሰለው ነገር መልኩን ቀይሮ ወደ ሌላ prophecies ወደተነገረለት ቦታ እየተመመ ነው።
የህይወት እጣ ፈንታ ጉዳይ ነውና ፕሮፌሲው ይፈፀም ዘንድ ቢላው ወልቃይትና ራያ ላይ እየተሳለ ነው። ያ ባይሆን ኖሮ በየትኛው የአለም የጦርነት ታሪክ በስንት መስዋእትነትና የሰው ህይወት የተያዘ ገዢ መሬት በተናጠል የተኩስ አቁም እወጃ ሙሉ ለሙሉ
ከያዘው ቦታ ለቆ ያቃል?
ዛሬ ጠቅላዩ በፓርላማ ስለዚህ ጉዳይ በሰጡት ትንታኔ ምእመኑ ረክቷል። ንግግራቸውንም እያጣቀሰ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ መለጠፍ ይዟል። የጠቅላዩን በሰባት አመታቸው ንጉስ ትሆናለህ ትንቢት ተቀብሎ ንጉስ ሆይ ሺ አመይ ይንገሱ
ያለ ማህበረሰብ የዚህ የጥፋት ክተት ዘመቻ ትንቢታዊ ትርጓሜውን አስልቶ ወደ አቅሉ ተመልሶ ለምን ሆነ ብሎ ይጠይቅ ይሆን? አብረን የምናየው ነው።

እስከዚያው ድረስ አማራ ወገኔ ሆይ? የጦርነትና የእልቂት ድግስ ወደ ቤትህ መቷል ምን ይሻልህ ይሆን?
ምን መላ ይገኛል ጦር ቢያከማቹት
አልገዛም ካለ ከወንድም ከሴት
ሸዋ ካልመከረ ይሆናል ወንፊት
እባብ መርዙን ከተፋ ይመጣል ፍጅት
ይህን እየሰማህ እንዳትገባ እሳት::
በድርቡሽ ሲገርመኝ የመተማ እልቂት
የማይጨው ሲገርመን የአድዋ ጦርነት
መቀሌን አየሁት አረሁ በልቶት
ሸዋ በገዛ እጁ በጫረው እሳት
ስንቱ ሰው ይነዳል ውቅሮ አዲግራት
አሥመራ ተወግቶ ወልቃይት መርዙን ተፋ
ሽሬና መቀሌ ይሆናል የከፋ
እንቅልፍ እንዳይወስድህ እርብ ሳይጠፋ
ይመስላል ላየው ሰው ቂያማ የተደፋ
እርብ ስንቱን ጣለው ጠብቆ ወረፋ::
ጋይንት ንፋስ መውጫ ድራና ፎገራ
እርብ ላይ ሞልቶ ሲዘፍን ሲያጎራ
ነጋዴው ይጮሃል መቀሌና አሥመራ
ምን ይበጀው ይሆን ጅልጋና ፎገራ?
ሸዋ ደፈረሰ እህሉን ሳይዘራ

ይሄንን እያሰብን ፖለቲካችንን መተንተኑ ምን ያጎልብናል? ምንም!!!
አይተ መለስ ዜናዊ በፅኑ ታመው አልጋ ላይ የዋሉ ጊዜ በአንድ ወቅት ስለ ወሎ ወያኔን ስላልመረጠ በአስተዳደር እየተበደለ ነው ተብለው ተጠይቀው "ወሎ የሸህ ሁሴን ጅበሪልን ትንቢት ቁጭ ብሎ ይጠብቅ" አንዳላሉ በህመም አልጋ ላይ በዋሉበት ወቅት
ሸሁ ስለወያኔ መጨረሻ ምን ብለው ይሆን ብለው የሸሁን ዘር ማንዘር ፍለጋ ወሎ ፍለጋ ሲማስኑ እንደነበር ሰምተናል።

ለማንኛውም ቢጠቅምም በይጠቅምም አጋራሁዋችሁ።

ወልቃትና ራያ ፈጣሪ ይሁንሽ!!!"

• • •

Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh
 

Keep Current with Mohammed Hassen

Mohammed Hassen Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

PDF

Twitter may remove this content at anytime! Save it as PDF for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video
  1. Follow @ThreadReaderApp to mention us!

  2. From a Twitter thread mention us with a keyword "unroll"
@threadreaderapp unroll

Practice here first or read more on our help page!

More from @Mohas0

4 Jul
It is always too late to rescue the politics of Ethiopia from descending into a catastrophic and tragic end at the expense of a generation opportunity in finding a better way to resolve political problems once for all. Time and again the public demonstrated an
unwavering interest and dream to have a national political change. A change that could emancipate him from the shackles of poverty, bad governance, and political crisis. It is the political elites who failed our people and our country.
Those political elites always used to hijack every political transition period only to ascertain their egoistic political interest than the public endeavor. When emperor Hailesselase was dethroned from power, there was an opportunity and shot. When Derg was overthrown,
Read 7 tweets
12 Nov 20
Thread!!!
=======
All eyes be on Raya !!!!
Attention Attention Attention !!!!

#TPLF completes preparations for genocide against #Raya people in #RAYA_ALAMATA front. It is expected to happen from tonight from November 13 to 15. A similar to the #Maikadera massacre is underway.
1) No Tigrayan national is currently in Raya Alamata.The last passengers were given 10,000 birr per person per day and left in big trucks to Tigray today.They were threatened to leave the city immediately & serious warnings given as to how to dismantle the city into barren land.
2) More than 600 Raya youths, investors and prominent elders were held prisoner at #Raya_Alamata Rural and Urban Woreda two police stations. It is said that there are many youths from Kidane, Garbe and 03 kebele among the prisoners. Other 50 militia men disarmed & imprisoned.
Read 8 tweets

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3/month or $30/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!

Follow Us on Twitter!

:(