ተጨማሪ
********
ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶችን አደንቃለሁ። የሁላችንም እገዛ ሊተከልበት ይገባል። ግልጽ ያልሆኑ ነገሮች ሲስተዋሉ መጠየቅ፣ እንዲሁም መፍትሔ መጠቆም መልካም ነው።
ቀደም ሲል ያነሳሁት ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጨማሪ ሃሳቦችን ልሰንዝር:-
1. ዜናውን ሳይ መጀመሪያ ጥያቄ የሆነብኝ:- ጉዳዩ ምርመራ ለማድረግ ከሆነ የታሰበው አቅሙ አለን? (የቁሳቁስ፣ የሠው ኃይል...)
2. ምርመራው ምን ያህል ጥልቀት ያለው ነው?
3. የተመረመረው ካልተመረመረው እንዴት ነው የሚለየው?
4. በቤት ለቤት ምርመራው ወቅት ሥራ ገበታቸው ላይ የሚገኙ ምርመራውን እንዴት ነው ሊያገኙ የሚችሉት?
5. ተጋላጭ ይሆናሉ የተባሉት ወረዳዎች በምን መስፈርት ነው የተለዩት? ወረዳዎቹስ እነማን ናቸው?
6. እንደዚህ አይነት መግለጫዎች ሲሰጡ የጤና ባለሙያዎችም ቢሳተፉ ጥሩ ነው። ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን እና ብዥታዎችን ሊያጠሩ ይችላሉ።
ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በየጊዜው ከትራምፕ ጋር በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጠውና ታዋቂ የህክምና ባለሙያዎችን ያካተተው የWhite House CoronaVirus Taskforce ነው።
ግብረ- ኃይሉ የሚሰጠው መረጃ የተብራራ ነው። የተወሳሰቡ ጉዳዮችን ብዙሃኑ በሚረዳው መልክ ያቀርባል።
ቸር ያሰማን።
መልካም ቅዳሜ።