My Authors
Read all threads
የፋሲካ ዕለት የሆነ ነው፡፡ ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ በፓትሮል የሚንቀሳቀሱ የፖሊስ አባላት አስኮ አዲስ ሰፈር አከባቢ ያደረጉት ድርጊት አስገራሚ ነው፡፡የአከባቢው ነዋሪ እስከዚህ ሰዓት ድረስ ምን እንደተፈጠረ እንኳ የሚያስረዳው አላገኘም፡፡ 1/8
በድንገት በሰፈሩ የተገኙት የፖሊስ አባላት በመንገዱ ላይ ያገኙትን ነዋሪ በሙሉ እያገላበጡ በዱላ መደብደብ ጀመሩ፡፡ ድብደባቸው ከፋፋይ አልነበረም፡፡ ሴት፣ ወንድ፣ ወጣት፣ አዛውንት ሳይል ያገኙትን በሙሉ መቀጥቀጥ ጀመሩ፡፡ 2/8
ድብደባው በዋና መንገድ ላይ ብቻ የተከናወነ አልነበረም፡፡በውስጥ ለውስጥ የኮብል ስቶን መንገዶች ላይ ሳይቀር ድብደባቸውን አድርገዋል፤በመንገድ ላይ ብቻቸውን ሲጓዙ የነበሩ ሰዎች ተደብድበዋል፡፡በዕድሜ ያረጁ ሽማግሌም ድብደባው ደርሷቸዋል፡፡3/8
የ8ወር እርጉዝ ሴት በፖሊስ ዱላ ድብደባ ተፈጽሞባታል፡፡ አዛውንቶች መሬት ላይ ወድቀው ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ወጣቶች ላይ የተካሄደው ድብደባ እጅግ አሰቃቂ እና ለመናገር ከባድ ነው፡፡መንገድ ላይ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን አሰልፈው ደብድበዋል፡፡4/8
የጸጥታ አካላቶቹ ድርጊት በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ የታጠቁትን መሳሪያ ተጠቅመዋል፡፡ 3 ጥይቶችን ወደ ህዝብ ተኩሰዋል፡፡ ወደ ሰማይ ሳይሆን ወደ ህዝብ ተኩሰዋል፡፡ ሆኖም የተተኮሰው ጥይት ያገኘው ሰው አልነበረምና የሰው ህይወት ሳያልፍ ቀርቷል፡፡5/8
አብዛኞቹ ተደብዳቢዎች ሲናገሩ የሰማሁት ግርምት ፈጥሮብኛል፡፡ የፖሊስ አባላቶቹ ከመጠን በላይ መጠጥ ጠጥተዋል፡፡ ገሚሶቹ የሚያደርጉትን ብቻ ሳይሆን የሚናገሩትን ጭምር አያውቁም ነበር፡፡ ከመጠጡ ብዛት የተነሳ የሚንተባተቡ ፖሊሶችም ነበሩ፡፡ 6/8
በድብደባው የተጎዱ በርካቶች ናቸው፡፡ በመንገድ ላይ ሲታዩ የሚያነክሱ፣ ከቤት መውጣትና መንቀሳቀስ የማይችሉ፣ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና የሄዱ ሰዎች እንዳሉ የዐይን እማኝ ሆኜ ታዝቤያለሁ፡፡ 7/8
የአካባቢው ህዝብ የተደበደበበትን ምክንያት አያውቅም፡፡ ያስረዳቸውም ሆነ ምክንያቱን የነገራቸው አካል የለም፡፡ ሆኖም በድብደባው የተጎዱ ሰዎች ክስ ለመመስረት እየተንቀሳቀሱ እንዳሉ ሰምቼያለሁ፡፡8/8
#Ethiopia
#StateOfEmergency
#covid19Ethiopia
Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh.

Enjoying this thread?

Keep Current with Tewodros Belay

Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

Twitter may remove this content at anytime, convert it as a PDF, save and print for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video

1) Follow Thread Reader App on Twitter so you can easily mention us!

2) Go to a Twitter thread (series of Tweets by the same owner) and mention us with a keyword "unroll" @threadreaderapp unroll

You can practice here first or read more on our help page!

Follow Us on Twitter!

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3.00/month or $30.00/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!