My Authors
Read all threads
በልምጭ ዲፕሎማሲ የኢትዮጵያን እጅ ለመጠምዘዝ መሞከሩ ድካም እንጂ ምንም አያመጣላቸውም:: በ2019 አሜሪካ ለኢትዮጵያ ያደረገችው ድጋፍ አጠቃላይ 1 ቢሊዮን ዶላር ነው:: አብዛኃኛው ለሰብዓዊ ተራድኦ የዋለ ነው:: አምባሳደሩ በግላቸው ተጨማሪ የእርዳታ 1/
ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ፈሰስ እንዲደረግና የትራምፕ አስተዳደርም ወደ ኢትዮጵያ ትኩረት እንዲያደርግ በዚያው ዓመት 3ጊዜ ወደ ዋሽንግተን ተመላልሰው: በአካል ተገኝተው ወትውተዋል:: አሁን ተከለከሉ እየተባለ የምንሰማቸውን ዘርፎች (ሴክተሮች) እንይ 2/
በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ መንግስት እርዳታ ተደርጎለት አያውቅም:: ከ2014-2018 ከdepartment of labor ለኬር ኢትዮጵያ 20 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ነበራቸው እንጂ ለመንግስት ቤሳቤስቲን ሰጥተው አያውቁም:: 3/
ለሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሊሰጡ ያሰቡት ትንሽ ገንዘብ ነበር:: እሱም ገና በእቅድና በንግግር ደረጃ ያለ:: ገንዘቡም ቢቀር በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ላይ የሚያመጣው ቅንጣት አሉታዊ ተፅእኖ አይኖርም:: 4/
በፀጥታ (የድንበርን ጨምሮ)ና ፀረሽብርና ድጋፍ የተባለውም አሜሪካ በቀጣናው ያላትን በርካታ ፍላጎቶች መሰረት ያደረገ እንጅ ኢትዮጵያ ሽብርንና የፀጥታ ስጋትን በራስዋ አቅምና ሃይል ስትከላከል የኖረች ሃገር ናት:ድጋፉ ቢቀር ከእኛ ይልቅ አሜሪካን 5/
ቢጨንቃት ነው:: ታገደ የተባለውን የገንዘብ መጠን ስናየው ደግሞ የተጠቀሰው መጠን አጠቃላይ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ መንግስት በዓመት ከምታገኘው 15% አካባቢ ነው:: ይሄ ምንን ያሳያል?
1.እንደተለመደው አሜሪካኖች ለታሪክ ግድ የላቸውምና መለስ ብለው 6/
የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ታሪክ አላገላበጡም::
2.ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ዲሪቶ ተብትቦ ያልያዛት በራስዋ ብቻ የምትንቀሳቀስና የምትወስን እውነተኛ ሉዓላዊት ሃገር መሆንዋን እያዩ እያወቁ አላወቁም ወይም እንደለመዱት እብሪት ጋርድዋቸዋል:: 7/
3.እናግዳለን ያሉት ገንዘብ ቢመጣም ባይመጣም ኢትዮጵያ ላይ የሚፈጥረው ለውጥ እንደሌለ ያውቁታል:: ግብፅን ላለማስቀየም ብቻ ሲባል ያደረጉት ሊሆን ይችላል::
4.የጉዳዩ ምንጭ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ሳይሆን ነጩ ቤተመንግስት (ፕሬዝዳንቱ) ነው:: 8/
በርካታ የወዳጅነት ክሮችን እንደሚበጣጥስና ከኢትዮጵያ ተኩዋርፎና ተቀያይሞ በምስራቅ አፍሪካ ያላቸው ገመድ እንደሚያሳጥር ያለማወቅ እና ግብዝነት ያለ ይመስላል
5.አዲስአበባ ያሉ ዲፕሎማቶች በጊዜው እንዲህ ያልተለመደና ያፈነገጠ ትእዛዝ ሲቀበሉ 9/
በአንድ በኩል መመሪያ የመፈፀም ጉዳይ በሌላ በኩል ደግሞ የፕሮፌሽናል የዲፕሎማሲ ስራን (professional integrity) በመጠበቅ መሃል አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ሲታገሉ የነበረ ቢሆንም አንዳንድ የዋህ ሃላፊዎች ግን የኢትዮጵያን እጅ መጠምዘዝ እንደሚችሉ 10/
ነበር የሚያስቡት::
6.የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት እንደ ፓወር አፍሪካ ባሉ initiatives ሊታገዝ ሲገባው አይን ያወጣ ከድህነት ጋር እንድንኖር ጫና መፍጠር ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ምን ማለት እንደሆነ አያውቁም!! 11/
7.ኢትዮጵያን በእንዲህ ያለ አካሄድ ለማሸማቀቅ መሞከሩ የእፍረት ማቅ ያከናንባቸዋል እንጂ ምንም ውጤት እንደማያስገኝላቸው ሚሊዮን ጊዜ አስረግጠን ነግረናቸዋል:: 12/
#ItsMyDam
#Ethiopia
Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh.

Keep Current with ሰላህ | Selah

Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

Twitter may remove this content at anytime, convert it as a PDF, save and print for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video

1) Follow Thread Reader App on Twitter so you can easily mention us!

2) Go to a Twitter thread (series of Tweets by the same owner) and mention us with a keyword "unroll" @threadreaderapp unroll

You can practice here first or read more on our help page!

Follow Us on Twitter!

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3.00/month or $30.00/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!