የምርጫ ታዛቢ የምርጫ ጊዜ ውሎ

የ6ተኛውን የኢትዮጵያ ምርጫን ለመታዘብ ፓርቲዬን ወክዬ ከተመደብኩበት የምርጫ ጣቢያ ከለሊቱ 11 ሰዓት ደረስኩኝ። የምርጫ ጣቢያው አስፈፃሚዎች በስፍራው ስላለነበሩ ከውጪ እንድንቆይ በፖሊሶች ተነገረን።

1/ብዙ
ስልክ መያዝ እንደማይቻል ነበር የነበረኝ መረጃ ስልኬን አልያዝኩም ሆኖም ሌሎች ታዛቢዎች እንደያዙ ስመለከት እኔም ስልኬን ለመምጣት ወደ ቤቴ ተመልሼ ስልኬን ይዤ ተመለስኩኝ። 11:45 ሲሆን አስፈፃሚዎቹ መምጣት ጀመሩ
2/ብዙ
የምርጫ ጣቢያው ሀላፊ ሲደርስ ሁላችንም በሰልፍ ሆነን ተፈትሸን ገባን።  ከኛ በኋላ ለመምረጥ የነበሩ እናቶች ሰልፍ መያዝ ጀመሩ። ወደ ምርጫ ጣቢያ ጊቢ ውስጥ ስንገባ ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉ ተነግሮን

3/ብዙ
ወደ ተመደብንበት ምርጫ ጣቢያዎቻችን ሄድን። ሀላፊው የጣቢያው ቁልፍ የተዘጋ እንደነበር ካሳየን በኋላ ከፈተው። እኛም ገብተን ቦታ ቦታችንን ያዝን። የታዛቢዎችን ስም እና ከምን ፓርቲ እንደመጡ መመዝገብ ጀመረ።

4/ብዙ
2 ሰው ከኢዜማ 2 ሰው ከብልፅግና 3 ሰው ከ አዲስ አበባ ወጣቶች ሊግ (አንደኛዋ ነፍሰጡር ነበረች)1 ሴትዮ ከየት እንደሆኑ አላወቁም የታዛቢ ባጅ ግን ይዘው ነበር የብልፅግናዋ ታዛቢ ደዋውላ ከህዳሴ ፓርቲ እንደሆኑ ነግራቸው በዛ መልኩ ተመዘገብን።
5/ብዙ
የምርጫ አስፈፃሚዎች አንዱ የምርጫ ቁሳቁስ የያዘውን ሳጥን ሙሉ ለሙሉ የተዘጋ መሆኑን አሳይቶን ቁጥር ያለባቸው የመዝጊያ ማሰሪያዎችን ካስመዘገበን በኋላ በመቀስ እየበጠሰ ከፈታቸው።

6/ብዙ
በውስጡ የሚገኙትን ሁሉም ነገሮች አንድ በአንድ እያወጡ አሳዩን። ሁሉንም የምርጫ እቃዎች ቦታ ቦታቸውን ካስያዙ በኋላ የምርጫ ድምፅ ወረቀት ማስገቢያ ሳጥኖችን ባዶ መሆናቸውን አይተን ቁጥር ባላቸው ማሰሪያዎች ከማስገቢያው

7/ብዙ
ክፍተት ውጪ ዘግተው የምን ምርጫ ሳጥኖች እንደሆኑ የሚገልፁ ወረቀቶችን ለጠፉባቸው። እኛም የማሰሪያዎቹን ቁጥሮች መዘገብናቸው።

በመቀጠል በእኛ ምርጫ ጣቢያዎች የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር በወንድ እና በሴት ተነገረን

8/ብዙ
አጠቃላይም 806 እንደሆኑ ከምርጫ መራጮች መዝገብ ላይ አየን።

በመቀጠል የመምረጫ ወረቀቶች ቁጥሮችን ስናይ ለህ/ተ/ም/ቤት 900 ለክልል ም/ቤት ደሞ 450 ነበር (በኋላ ላይ ቀሪው 450 መጥቶ ተሞልቷል)።

10/ብዙ
የተለያዩ ድምፅ መስጫ ወረቀቶች እንደነበሩም አየን የሁሉም ተወዳዳሪ ዕጩዎች እንዳሉ አየን። የመምረጥ ሂደቱ ካለቀ በኋላ በቆጠራ ላይ የሚኖሩ አለመግባባቶችን እንዴት እንደምንቀርፍ ቀድመን ተወያየን

11/ብዙ
ምን አይነት ምልክቶች እና ወረቀቶች ድምፅ እንዳላቸው እና ድምፅ አልባ የሚሆኑት ሁኔታ ላይ ከተወያየን በኋላ በቃለ ጉባኤ ላይ መስማማታችንን በፊርማችን አረጋገጥን።
ለመራጮች ማሳያ የሆኑ ውጪ ላይ የሚለጠፉትን አስፈፃሚዎቹ ከለጠፉ

12/ብዙ
በኋላ መራጮች በሰልፋቸው መሰረት ተፈትሸው እንዲገቡ ተፈቀደ። ይህ ሲሆን ሰዓቱ 12:45 ሆኖ ነበር።

እኔ የተመዘገብኩት እዚሁ ጣብያ ላይ ስለነበር ሰው ሳይበዛ ለመምረጥ እንዲሁም የአመራረጥ ሂደቱን ከጅምሩ

13/ብዙ
ለመገምገም የመጀመሪያው መራጭ ሆንኩኝ። የመጀመሪያው አስፈፃሚ በመዝገቡ ላይ ስሜን ፈልጎ ከመታወቂያዬ እና ከ ምርጫ ካርዴ ጋር አስተያይቶ በስሜ ትይዩ እንድፈርም አሳየኝ ፈረምኩለት ቀጥሎ በግራ እጄ አውራ ጣት ላይ

14/ብዙ
የመራጭነት ማረጋገጫ ቀለም አደረገብኝ እንዴት መምረጥ እንደሚቻል ሌላኛው አስፈፃሚ አሳየኝ። የህ/ተ/ም/ቤት እና የአ.አ ም/ቤት ምርጫ ወረቀት እንደሚለያይ አሳየኝ እዛው ላይ ያለኝ ቅሬታ አሳወኩት

15/ብዙ
ይህም የአ.አ ም/ቤት መምረጫ ወረቀቱ አራት ገፅ እንዳለው እንዲያብራራ ነበር እሱም ወዲያውኑ ከኔ ለመጡ መራጮች አረዳዱን አስተካከለ። እኔም ወደ ምንመርጥበት ሳጥን ሄጄ የምፈልገውን ምርጫዎቼን አስፍሬ

16/ብዙ
ወደ ምርጫ ወረቀት መቀበያ ሳጥኑ አመራሁ እዛ ጋር ስሄድ ደሞ ሌላኛው አስፈፃሚ የህ/ተ/ም/ቤት ማስገቢያው ሳጥን ውስጥ የህ/ተ/ም/ቤት ወረቀቱን እንዲሁም የአ.አ ም/ቤት ምርጫ ሳጥን ውስጥ ደሞ የአ.አ ም/ቤት ምርጫ

17/ብዙ
ወረቀትን አጣጥፌ እንድከት አሳይቶኝ እኔም እዳለኝ አደረኩኝ።

ይሄን ቅደምተከተሎች በመከተል መራጮች በአመጣጣቸው ቅደም ተከተል (ከአቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኞች በስተቀር) ወደ ምርጫ ጣቢያው በመግባት ሲመርጡ ዋሉ።

18/ብዙ
የመረጣ ሂደቱ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ነው የዋለው ዝናብ የመጣበት ሰዓት ላይ ብቻ ውጪ የተሰለፉትን ሰዎች ወደህንፃው እና ወደ ድንኳን ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ የተፈጠሩትን የሰልፍ ችግሮች በነበሩት የፀጥታ አስከባሪዎች ወዲያውኑ ተቀርፏል።

19/ብዙ
በመመገቢያ ሰዓቶች የምርጫ ታዛቢዎች በየተራ እየሄዱ የተመገቡ ሲሆን እኔ እና አብራኝ የነበረችው የኢዜማ ታዛቢ ግን ለግብዣው ፈቃደኛ አልነበርንም ምሳ ሰዓት ላይ በየ ተራ ለ 1 ሰዓት እቤታችን በመሄድ አርፈን እና በልተን ግን ተመልሰናል

20/ብዙ
በዚህ ሁኔታ የቀጠለው የመምረጥ ሂደት እስከ 12 ሰዓት ድረስ ቀጠለ በመሃል ላይ የአ.አ ም/ቤት ምርጫ ሳጥኑ ስለሞላ በማሰሪያ ታስሮ በአዲስ ተቀይሯል። 12 ሰዓት ሲሆን የምርጫ ጣቢያው ሀላፊ ሰልፍ ላይ ከነበሩት ውጪ ተጨማሪ መራጮች

21/ብዙ
እንዳይሰለፉ ብሎ ለፀጥታ ሃላፊዎች መልዕክት አስተላለፈ። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ተዘዋወሪ የምርጫ አስፈፃሚ የነበረ ሰው መጥቶ እስከ 3 ሰዓት እንደ ተላለፈ ለሁላችንም አረጋገጠልን። በዚህ ጊዜ ላይ 635 መራጮች መርጠው ነበር

22/ብዙ
የተራዘመው ሰዓት ሲያልቅ ደሞ 658 መራጮች መርጠው ሄደዋል።
የተጨመረው ሰዓት እንዳለቀ የምርጫ ጣብያው በር ተዘግቶ የመምረጫ ሳጥኖች በቁጥር ባላቸው ማሰሪያዎች ታሰሩ። የመቁጠር ሂደቱ 3:25 ሲል ተጀመረ።

23/ብዙ
በቅድሚያ ስንት ሰው እንደመረጠ ከመራጮች መዝገብ ላይ አየን እዛ ላይ እንደሚለው 150 ሰዎች እንዳልመረጡ 556 ሰዎች እንደመረጡ ነው።
ቀጥሎ የህ/ተ/ም/ቤት ምርጫ ወረቀቶችን የያዘው ሳጥን ሙሉ ለሙሉ ጠዋት ላይ በተዘጋባቸው ማሰሪያዎች ተዘግቶ

24/ብዙ
እንደነበር ካየን በኋላ የምርጫ አስፈፃሚው ቆርጦ ከፈተው። በውስጡ የነበሩት ድምፅ መስጫ ወረቀቶች ስንቆጥር 658 ሆነው ተገኙ ከመራጭ መዝገቦች ጋር ስናስተያይ በሁለት በልጦ ተገኘ በድጋሚ የመራጭ መዝገቡ እና ወረቀቶቹ ተቆጠሩ

25/ብዙ
አሁንም ልዩነቶች ተፈጠሩ በቃለ ጉባኤው ተይዞ ሁለት ሰዎች በመራጭ መዝገብ ላይ ሳይፈርሙ እንደመረጡ ተደርጎ እንዲወሰድ ተስማማን። ከዛም መቁጠር ሂደቱ እንዴት እንደሚሆን በማሳየት እና በሚታይ ሁኔታ ላይ ሆነን ሁላችንም

26/ብዙ
እንድንመዘግብ ሆኖ የቆጠራው ሂደት ተጀመረ። ቆጠራው ሲጠናቀቅ በሁሉም በኩል እኛ ከያዝነው ቁጥር ጋር ተመሳስሎ ነበር ከብልፅግና ውጪ። አስፈሳሚው ከቆጠረው እኛ የቆጠርነው ጋር በ3 መራጭ የተለያየ ሆኖ ተገኘ።

27/ብዙ
የምርጫ አስፈፃሚ ሀላፊውም ድጋሚ መቆጠር እዳለበት አሳወቀን። ይህ ሲሆን ሰዓቱ ከሌሊቱ 6ሰዓት ሆኖ ነበር። ድጋሚ ቆጥረን ሙሉ ለመሉ ተመሳሳይ የሆነ ውጤት ላይ ስንደርስ የምርጫ ወረቀቶቹን ሰብስበው በ 50 50 ተደርገው ታስረው

28/ብዙ
በሳጥን ውስጥ ገብተው ተዘጋ። ይህን ስንጨርስ ሰዓቱ ወደ ከሌሊቱ 9 ሰዓት እየተጠጋ ነበር።

የአ.አ ም/ቤት ምርጫ ወረቀቶችን ስንቆጥር ደግሞ 659 ሆኖ ተገኘ ይህንንም በቃለ ጉባኤው ተይዞ ሶስት ሰዎች በመራጭ መዝገብ ላይ ሳይፈርሙ እንደመረጡ

29/ብዙ
ተደርጎ እንዲወሰድ ተስማማን።

ይህ የቆጠራ ሂደት ከሚቆጠረው ድምፅ ብዛት፣ ከድካም እና ከእንቅልፍ መደራረብ ጋር ሆኖ እጅግ ከባድ ነበር። አንድ በአንድ እየቆጠርን ነጋ ቁርስ ሰዓት ላይ ሁሉም በምርጫ ጣቢያው የተዘጋጀውን ምግብ ሊበሉ

30/ብዙ
ሲወጡ እኔ እና የምርጫ ጣቢያው ሀላፊ በዛው ቀረን። ተመልሰው ሲመጡ ቆጠራውን ቀጥለን 7 ሰዓት አካባቢ አገባደድን። የያዝናቸውን የምርጫ ውጤቶች ስናመሳስል ተመሳሳይ ሆኖ አግኝተነው። ቆጠራውን ፈፀምን።

31/ብዙ
ከዛ በኋላ የሚሞሉ ፎርሞችን ሞልተው ፈረምን የጣብያውን ውጤት ለህዝብ በሚታይ ቦታ ላይ ተለጠፈ። እኛም ስለ ሂደቱ የነበረውን ነገር ከተወያየን በኋላ ቃለ ጉባኤው ላይ ፈርመን ወደየቤታችን ሄድን።

32/ብዙ
አጠቃላይ የምርጫ ቀን እና ቆጠራ ሂደቱ ላይ ምንም አይነት የማጭበርበር ሙከራዎች አልነበሩም። ሂደቱም ሰላማዊ እና ግልፅ ነበር።

አሁንም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምስጋና እና አድናቆቴ ይድረሳችሁ። @NEBEthiopia

33/ብዙ
የእኛ የምርጫ ጣቢያ ውጤቶች እንደዚህ ናቸው 👇🏾👇🏾👇🏾።
የተወካዮች ምክር ቤቱን @dagmawit_moges አሸናፊ ሆናለች።
33=ብዙ

• • •

Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh
 

Keep Current with በአንተአምላክ | Beantamlack ⛹🏾‍♂️⚖

በአንተአምላክ | Beantamlack ⛹🏾‍♂️⚖ Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

PDF

Twitter may remove this content at anytime! Save it as PDF for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video
  1. Follow @ThreadReaderApp to mention us!

  2. From a Twitter thread mention us with a keyword "unroll"
@threadreaderapp unroll

Practice here first or read more on our help page!

More from @yefelekebay

20 Jun
We done it again!!!
AAU won 71 - 60 against B4L

Defended the title 😁
#Repeat
So proud of you all!

And for those of you who came to support me, thank you ot really means a lot!❤ ImageImage
Some pics from the game👇

Caught in action 😁 Image
Team mates 🧡 Image
Read 6 tweets
14 May 20
@ZemenuYA So basically Rotract is part of the worlds largest voluntary organisation called Rotary.
It is the youth part of this organisation. Starts from age 18 and used to be until 30, but as off last year that above age limit has been withdrawn.
@ZemenuYA So in Rotaract members (Rotaractors)are expected to develop their professional skills while giving back to the community.
They can develop their skills through different means,
1. There are different leadership positions so one can be elected and serve at a one position for 1yr.
@ZemenuYA 2. You network with professionals from different backgrounds. In Ethiopia there are 16+ Rotaract clubs, each have members from different professions.

3. There are trainings organised by the clubs them selves. Well known Guest speakers will be invited and will share experiance
Read 15 tweets

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3/month or $30/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!

Follow Us on Twitter!

:(