Thread 1
"..ሳይቀድሙን እንቅደም.."
ጦርነት እንዴት ተጀመረ? የሚለዉን የቀድሞው ብአዴን: የአማራ ክልል ተወላጅ የሆነው ህወሓት ጌታቸው ሴኩቱሬ እቅጩን ነግሮ ገላግሎናል። ህወሓት "ሳይቀድሙን እንቅደም" ብሎ ይህን ለምን እንዳደረገ የኔ ሀሳብ ይህ ነው Image
Thread 2
ኢህአዴግ "ራሳችንን ማጥራት ያስፈልገናል ፣ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በውስጣችን የነቀዙ (corrupt) ግለስቦችን ከአራቱም ፓርቲዎች ለህግ እንድናቀርብ ይሁን" ብለው ተስማምተው የአሁኑን 'ጠቅላይ ሚኒስትር' መርጠው ህወሓት አላቸው የተባለውን
Thread 3
ተጽእኖ ሁሉ አዲስ ለተመረጠው አካል ሰላማዊ በሆነ መንገድ ባስረከቡበት ሁኔታ ፣ ውግዘቱ ፣ ማስፈራራቱ መሳደዱ ግን ከአራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች ( ህወሓት/ብአዴን/ደህዴን/ኦህዴድ) ይልቅ የበረታው በህወሓትና በሚወክለው ህዝብ ላይ ነበር
Thread 4
በስምምነታቸው መሰረት ንቁዝ ባለስልጣናት ወደ ፍርድ እንዲቀርቡ ሲጀመር የትግራይ ልዮ ሀይል በሁመራ ሜ/ጄ ክንፈ ዳኘውን በህጉ መሰረት ለፌደራል ሀይል ሲያስረክብ እጅግ አዋራጅ በሆነ መልኩ ያልተፈረደበት ተጠርጣሪ በቢጫ ሄሊኮፕተር..
Thread 5
(በሁዋላ ሄሊኮፕተሯ የ"ወንጀለኛ" ማስፈራርያ ስላቅ ምልክት ሆናለች) በማጓጓዝና በተጋነነ የሚዲያ ሽፋን እኒሁኑ ያልተፈረደባቸውን ተጠርጣሪ አስታኮ የትግራይን ህዝብ አንገት ማስደፊያና ነጥሎ ማጥቂያ በቴሌቭዥን በሚሰሩ "ዶክመንታሪዎች"..
Thread 6
"..ትግርኛ ተናጋሪ.." በሚሉ ቃላት ህወሓትን ብቻ ሳይሆን የትግራይን ህዝብ በጥርጣሬ ማገንገን ጀመሩ። 'ጠቅላይ ሚኒስትሩ' ሳይቀር 'የቀን ጅቦች' ፣ 'ጸጉረ ልውጥ' በሚሉ የሾርኒ (dog whistle) ቃላት ማስጠቂያ እና አንገት ማስደፊያ ዘዴ መጠቀም ያዙ
Thread 6
ቀደም ሲል እንዳነሳነው ሁሉም የኢህአዴግ ድርጅቶች (ህወሓት/ብአዴን/ደህዴን/ኦህዴድ) በውስጣቸው ያሉትን ንቁዛን እንዲያስረክቡ ተስማምተው ስልጣን ለአሁን 'ጠቅላይ ሚኒስትር' ቢያስረክቡም፣ ታሳሪ የሚፈለገው ከህወሓት ብቻ ሆነ። በሌሎቹ..
Thread 7
ድርጅቶች የነበሩ ንቁዛን ከነጭራሹ ከፍተኛ ቁልፍ ባለስልጣናት አለያም "አምባሳደሮች" እየሆኑ ተሾሙ። ይህንን ምክንያት አድርጎ ህወሓት ተጠርጣሪዎችን በተደጋጋሚ ስሙ የሚነሳውን "ጌታቸው አሰፋን" ሳይቀር ለፌዴራል መንግስት ለማስረከብ..
Thread 8
ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ። በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የምዝበራ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ እነ አባዱላ ገመዳ በክብር እያሉ ትግራዋይ ባለስልጣናት የነበሩ ብቻ መታደን በህወሓት ሆነ በትግራይ ህዝብ የመከበብ የመገለል ስሜት እንዲፈጠር Image
Thread 9
ምክንያት ሆኗል። ይባስ ብሎ ግን ፍጹም አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እስካሁን ለምንና እንዴት እንደሆነ ባልታወቀ መልኩ የኢትዮጵያ መከላከያ ኤታ ማጆር ሹም ጄኔራል ሰዐረ መኮንን በመኖርያ ቤታቸው እንደነበሩ ተገደሉ። እስከ ዛሬዋ ሰዐት ድረስ.. Image
Thread 10
ገዳያቸው ጠባቂያቸው ነው ከሚለው ብዥ ያለ ሰበብ በስተቀር የገዳያቸው ፍርድ ሂደትና ዝርዝር ሁኔታ ፈጽሞ አይታወቅም። በዚህ ሁኔታ የትግራዎት በመከላከያ ውስጥ የነበረ አስተዋጽኦና ተጽእኖ መጥፋቱ የህወሓትንና ትግራዎት ጥርጣሬ አባባሰው
Thread 11
የኢትዮጵያ የህዝቧና በተለይ የትግራይ ህዝብ ፍጹም ደመኛ የሆነው ኢሳያስ አፈወርቂ ቤተኛ መሆን ከነጭራሹ ባደባባይ 'በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ያስፈልገናል' ብሎ መናገር በየጊዜው "ጨዋታው አብቅቷል" (Game over) እያሉ ማወጅ የህወሓትንና Image
Thread 12
የትግራይን ህዝብ ጥርጣሬ ካገነገኑት ምክንያቶች ዋንኛው ነው። የአማራ ክልል መንግስት መሳፍንት የሚባል ሽፍታ 'ትግራይን ሄጄ እጨብጣታለሁ' ሲል "ተው እንዲህ አይባልም" ብሎ አደብ ከማስገዛት ይልቅ ይህንኑ ሽፍታ በጸጥታ መዋቅሩ ሾመ። Image
Thread 13
'ጠቅላይ ሚኒስትሩ' ለትግራይ ህዝብ ስር የሰደደ ጥላቻና መርዘኛ አመለካከት ያላቸውን እንደነ @ETHZema ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶችንና እንደነ ብርሀኑ ነጋና አል ማርያም አይነቶችን ለህዝብ ፋሽስታዊ አመለካከት ያላቸውን ግለሰቦች ባቅራቢያው ImageImageImage
Thread 14
በማድረጉ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ በፌዴራል መንግስቱ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ ይበልጥ አገነገነው። ወደ ትግራይ ለመጓዝ የፈለጉ ኢንቬስተሮች ወይም ወደ ትግራይ የሚጓዙ አንዳንድ ሰወች የመከልከል የመዋከብ ሁኔታ ማጋጠም የአብይ መንግስት..
Thread 15
ክፉ እያሰበ እንዳለ የሚያጠራጥሩ አመላካቾች ነበሩ። የትግራይ ክልል ምርጫ አደርጋለሁ ብሎ ሲነሳና (በወቅቱ ይህንን እኔም ተቃውሜያለሁ) ምርጫው ከተደረገ በሁዋላ በአነስተኛ ፓርላሜንታዊ ቅጣት (wrist slap) ከመቅጣት ይልቅ በጀት መከልከል
Thread 16
የአብይ መንግስት ትግራይን ለመጨፍለቅ ያለውን እቅድ ከሚያሳዩ ግዙፍ ምልክቶች አንዱ ነበር። በሀገሪቱ ውስጥ ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት ሆኖ 46 አመት የቆየ ድርጅት ህወሓት ነው። የፖለቲካ አተናተን የውትድርና ሳይንስ በዚህ ግማሽ ምእተ ዓመት
Thread 17
..ሊሞላ ትንሽ በቀረው እድሜው ያካበተ የህዝብ ድጋፍ ያለው ድርጅት ነው። ይህንን ሀይል በዘዴ በመግባባት በመተማመን ነው እንጂ "እሸውደዋለሁ" "እስፈራራዋለሁ" በሚል እሳቤ ለመጨፍለቅ መሻት ይህንን እያየን ያለነውን ጥፋት ያስከትላል።
Thread 18
በነዚህ ከላይ በዘረዘርኳቸው ምክንያቶች ሁሉ በሀይል እንዲጠፋ እየተደገሰለት መሆኑን የተገነዘበው ህወሓት ህዝቡ ከሁዋላው እንደሚሆን በምርጫ አይቶ በማረጋገጡ ቀደም ባሉት ቀናት ደግሞ ከኤርትራ መንግስት በወጣ መግለጫ ዛቻና ማስፈራርያውን
Thread 19
እንደ ጦርነት አዋጅ በመውሰድ ይህንን እርምጃ በሰሜን እዝ ላይ የወሰደ ይመስላል።
ከሰሜን እዝ ውስጥ ቁጥሩ ቀላል የማይባል ከትግራይ ልዮ ሀይል ጋርም እንዳበረ አሁን ከፈረጠመው ጉልበቱ መረዳት ይቻላል።
Thread 20
የሆነው ሆኖ ግን ወደፊት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የምትኖረን ከሆነ ይህ መጥፎ ምሳሌያዊ አመላካች (bad precedent) ነው። በክልል ያለ ሀይል በክልሉ ውስጥ ያለውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የሚያባብለውን አባብሎ የሚያስገድደውን አስገድዶ..
Thread 21
ጦርነት የሚጀምር ከሆነ እርስ በርስ መተላለቃችን ነው። የህወሓትንና የትግራይን ህዝብ ጥርጣሬና ምክንያት ብረዳም ይህ ለወደፊት የሚፈጥረውን ምሳሌ ሳስበው እጅግ ይዘገንነኛል። በመሆኑም አሁንም ጦርነት ይቁም #SayNoToWarEthiopia እላለሁ
Thread 22
እንደተለመደው በጨዋ መልክ የሚቀርብ ከስድብ ከግል ማብጠልጠልና ከዘረኝነት የጸዱ ሀሳቦችንና መልእክቶችን ብቻ ነው የማስተናግደው። አመሰግናለሁ።

• • •

Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh
 

Keep Current with Naty Yifru (ናቲ ይፍሩ)

Naty Yifru (ናቲ ይፍሩ) Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

PDF

Twitter may remove this content at anytime! Save it as PDF for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video
  1. Follow @ThreadReaderApp to mention us!

  2. From a Twitter thread mention us with a keyword "unroll"
@threadreaderapp unroll

Practice here first or read more on our help page!

More from @Natberh

19 Feb
Thread 1
A lesson to the barbaric #UnityForEthiopia club.
These are same people whose churches & mosques you desecrated, raped, murdered, looted. Yet, when #Tegaru capture mostly naive, child soldiers you sent to do these things, #Tegaru see them as what they are. Human beings.
Thread 2
These young people, have been driven to war for your fascistic goal & unquenchable thirst to rule over others. You forced them to kill their brothers, rape their sisters, desecrate their churches & mosques. You made them POW in their own country.
Thread 3
As you see in these clips, no matter how much your crimes are unspeakably fascistic and barbaric in #Tigray, your barbarism is not being paid in kind. Learn from these civilized folks you intend to destroy! #Ethiopia
Read 4 tweets
19 Feb
Dear @befeqe
Thread 1
It's important to learn from history of the world that fascists NEVER win. They wreck havoc. They kill (Oh boy! do they know how to kill?) But, there is NO WHERE in history, where they won. When they lose, they lose in a fantastically humiliating manner!
Thread 2
Just like only flag colors & Teddy Afro song brings your lot together, they loved symbolism (The Swastika, the lifting left hand high salute the flag etc.) That is because other than those emotion triggering trivial matters, there's very little that brings them together.
Thread 3
Their HUGE commonality was HATE! In the case of Nazis, for example it was the hate of Jews most of all. And they came up with all sort of "creative" way to murder & torture Jews. Just like you came up with horrific kind of rape, looting and murdering #Tegaru
Read 6 tweets
21 Nov 20
Thread 1
ኢትዮጵያ ነገ:-
ለብዙዎቻችንን ድንገቴ በሆነ ሁኔታ የዛሬ ሶስት ሳምንት ሀገራችን ኢትዮጵያ በግትርና በማን አለብኝ መሪዎቿ (በሁለቱም ወገን) የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቃለች። እንደ እኔ እምነት ይህ ጦርነት እንዳይሆን ማደረግ..
Thread 2
የሚቻልባቸው በርካታ መንገዶችና ያመለጡ እድሎች ነበሩ። ይሁንና ስለፈሰሰ ውሀ መብስልሰሉን ትተን ነገ በምን ሁኔታ ሀገራችንን መታደግ እንደምንችል መነጋገር ብንጀምር አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ።
Thread 3
የጦርነት ዋጋ:-
በአለም ላይ በተደረጉ ሁሉም ጦርነቶች እንደታየው መጀመርያም መጨረሻም ላይ በአካል በምጣኔሀብት በስነልቦና የሚጎዳ ሰላማዊ ህዝብ እንጂ ተፋላሚ ጦር አንጋቾች አይደሉም። በተለይ በዚህ ጦርነት ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ..
Read 24 tweets
8 Nov 20
Thread 1
ይህ ቅጥልጥል በአሳዛኝ ሁኔታ የኢትዮጵያ የስልጣኔ መሰረት የሆኑትን ሰሜን ኢትዮጵያውያንን አፋጅቶ ለማዳከም በ "ብልጽግና ወንጌል" ፖለቲካዊ የሀይማኖት ርእዮተ ዓለም በ @AbiyAhmedAli ጦርነት ሰለታወጀበት የኢትዮጵያ ክፍል #ትግራይ ነው Image
Thread 2
እኛ ኢትዮጵያዊያን የ3ሺ ዘመን ታሪክ አለን ብለን የምንመጻደቅበት አክሱም ፣ የኢትዮጵያ ስርወ መንግስት አሰራር (State Craft) እና የስልጣን ተዋረድ (Hierarchy) ጥንስሱ የተጀመረበት የማንነታችን መነሻ ያለው አክሱም ትግራይ ነው። Image
Thread 3
ከአውሮፓውያን ቀድማ ከአብርሀማዊ እምነቶች አንዱ የሆነውን ክርስትናን የተቀበለችው ኢትዮጵያ ለመሆኗ የምትመስክር በኢትዮጵያ ተዋሕዶ አማኞች እንደሚታመነው አምላክ ለሙሴ የስጠው የአስርቱ ትእዛዛት ጽላት ያረፈበት አክሱም ትግራይ ነው። ImageImage
Read 20 tweets

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3/month or $30/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!

Follow Us on Twitter!