, 12 tweets, 3 min read
My Authors
Read all threads
Thread

#ታምራትነገራ #ትምክህት #ንቀት #አሐዳዊነት #ጥላቻ #ኢትዮጵያ #ኤርትራ

ኢትዮጵያን ወዶ ሕዝቦቿን የሚጠላው ልጅ!

«በኢትዮጵያ ጉዳይ ከእናቴ ልጅ ጋርም አልደራደርም» ይልሃል… ልጅ ታምራት ነገራ። የሚወዳት ግን ሙሉይቷን ኢትዮጵያ አይደለም!👇
👉ብሄር ብሄረሰቦችን እንደጉድ ያጥላላል። ሲፈልግ ዝንጀሮ፣ ሲፈልግ ጦጣ ያደርጋቸዋል። ወረቀት ላይ የሠፈሩ ጽንሰ ሐሳቦች እንጂ እንደእሱ አጥንት እና ደም ያላቸው የሰዎች ስብስብ አይመስሉትም። 👇
👉ለሰዎች የባህልና የቋንቋ እሴት የጥፍሩን ቆሻሻ ያክል አይጨነቅም። ምክንያቱም እሱ ከራሱ «ከተሜያዊ» ማንነት ውጭ ለማንም ክብር የለውምና። ሲሳደብ እና ሲያንቋሽሽ እስከጥግ ነው። 👇
👉የሰዎች መከራ፣ ብሶት፣ ቁጭት ለእሱ ምኑም አይደለም። በሰው ቁስል እንጨት መስደድ እጅጉን ይመቸዋል። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሕወሓትን ሁለንተናዊ ዘመቻ ለመታገል ደማቸውን ሲያፈሱ እሱ በጽሑፎቹ ይሳለቅ ነበር። ማስመቻ ጽሑፍ ይጽፍ ነበር። 👇
👉የሕወሓትን የአክራሪነት ካርድ እየመዘዘ ያላግጥ ነበር። የሙስሊም ጥላቻው እስከአንገቱ ነው — ምክንያቱም ለእሱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ብሄራዊ ስሜት የሌላቸው ነጭ ለባሾች፣ ለአገራቸው የማይታመኑ ባንዳዎች ናቸው።👇
👉ደስ ሲለው «ኦሮሚያ መበታተን አለባት» ይልሃል፤ ስለአንድ ክልል ሳይሆን ስለjigsaw puzzle የሚያወራ ይመስል! የብዙዎችን ስሜት እንደሚያቆስል እያወቀ «ኦሮሞ ምኒልክን ማምለክ ይገባዋል» ይልሃል። የሕዝብ መናደድ የሞራል ሥንቁ ነው። 👇
👉ልጁ ፃፃ የለውም! ያሻውን ይዘረጥጣል! ጅንፍልና የሚያስገኘው አቴንሽን ይጣፍጠዋል። ጨዋ የዱሮ ጓደኞቹ ይሸሹታል። በሚዲያ አብረውት አይቀርቡም። እነሱንም የሚያሳቅቅ «ላያቢሊቲ» መሆኑን ያውቃሉ። ጠላት ፈልፋይ ልቅ አንደበቱን ይፈራሉ።👇
👉ደስ ሲለው ስለነፃነት እና ዲሞክራሲ ያወራል። መልሶ ኤርትራውያን በአምባገነን መሪ ሲሰቃዩ መኖራቸው እንደሚያስደስተው ይነግርሃል። ለ30 ዓመታት ለሞት፣ ለእስር፣ ለስደት የተዳረጉት ኤርትራውያን መስዋዕትነት ለሱ የደስታ ምንጩ ነው። 👇
👉ጨቋኛቸውን «ስለጨቆነልን ልናመሠግነው ይገባል» ይልሃል። እንደውም «ኤርትራን ለማቆርቆዝ እንተባበር» ሊልህ ሁሉ ይችላል። ለጎረቤት ክፉ መመኘት፣ ያውም በእርቅ ከተቃቀፍከው ጎረቤትህ ጀርባ ጩቤ መቀርቀር እንደሚያስፀይፍ አይገባውም። 👇
👉ልጁ ፃፃ የለሽ «ከተሜ» ነው። ኢትዮጵያን «ይወዳል»… ያውም በጣም! ግን ዲሞክራሲ እና ሰብዓዊ መብት እንደሚበዛባት ያስባል። አፉን ሞልቶ ምርጫው መጭበርበር እንዳለበት ይነግርሃል። የሕዝብ ምርጫ ለእሱ ምኑም አይደለም… «አራዳ ከተሜ» አይደል!👇
👉ሼም አያውቅም። ያሻውን ይናገራል። ያሻውን ይዘረጥጣል። ምናለበት ቢዘረጥጥ! ኢትዮጵያን ይወድ የለ!? በኢትዮጵያ መደራደር አያውቅም አይደል!

እንዲህ ዓይነት ሰዎች በየቦታው አሉ — ኢትዮጵያውያንን ጠልተው ኢትዮጵያን «የሚወዱ»! 👇
👉አገሪቷን ወደው በውስጧ ያለውን የሚንቁ! ሕዝቧን ጠልተው ጋራዋን የሚያፈቅሩ! ብዝኃነቷን ጠልተው የካርታ ስፋቷን የሚያደንቁ!

ኢትዮጵያን ከልበ-ጠባቦች መዳፍ ፈልቅቆ ብዝኃነቷን ማወጅ፣ የሁልነቷን ማረጋገጥ የእኛ ሥራ ነው! እህሳ…እጃችሁ ከምን…!?
Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh.

Enjoying this thread?

Keep Current with Isaac Eshetu

Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

Twitter may remove this content at anytime, convert it as a PDF, save and print for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video

1) Follow Thread Reader App on Twitter so you can easily mention us!

2) Go to a Twitter thread (series of Tweets by the same owner) and mention us with a keyword "unroll" @threadreaderapp unroll

You can practice here first or read more on our help page!

Follow Us on Twitter!

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just three indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3.00/month or $30.00/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!