———
የአዲስ አበባ መሥተዳድር በታሪኩ ሊያፍር ይገባል!
———
.
የአፍሪካ መዲና የሆነችው #አዲስአበባ አሥተዳደር በታሪኩ ወርድ እና ቁመት ልክ በበደል ክምር ላይ ተጠፍጥፎ የተጋገረ አሳፋሪ መሥተዳድር መሆኑን የምታውቀው ከተማው ውስጥ👇
👉የሙስሊሙ ማኅበረሰብ የአምልኮ ቦታ አሰጣጥ ቢሮክራሲያዊ ሂደት ምን ያክል ፍትህ አልባ እና የዜግነት ክብር የነፈገ መሆኑን ስታይ ነው። ከምር እጅግ ያሳፍራል!👇
👉ከተማዋ ውስጥ እያንዳንዱ ሃይማኖት በአማካይ ለአንድ የአምልኮ ቦታ የሚደርሰውን ቦታ ስፋት ተመልከቱ። ዛውያ ቲቪ ባጠናቀረው ጥናታዊ ፊልም ላይ በተጠቀሰው ዳታ መሠረት በአዲስ አበባ...👇
⛪️ የ1 የኦርቶዶክስ ቤ/ክ አማካይ ስፋት 21200 ካሬ ሜትር ነው

☦️ የ1 የፕሮቴስታንት ቸርች አማካይ ስፋት 4438 ካሬ ሜትር ነው

✝️ የ1 የካቶሊክ ካቴድራል አማካይ ስፋት 3473 ካሬ ሜትር ነው
.
🕌 የ1 መስጊድ አማካይ ስፋት 1292 ካሬ ሜትር ነው 😓👇
👉«ለምን የሌሎች ሃይማኖቶች ተፈቃጅ ይዞታ ሰፋ?» አይደለም ጥያቄው። ምናለበት! ይስፋቸው! ምችት ይበላቸው! የአገር ልጅ ምቾት የራስ ምቾት ነው። 👇
👉ጥያቄው «ሙስሊሙ በአምልኮ ቦታ እጦት በየአስፋልቱ እየሰገደ እስከመቼ ይኖራል? ለምንስ በቢሮክራሲያዊ መድልዎ የአምልኮ መብቱን ይነፈጋል?» ነው! በፍትህ ላይ ያልቆመች ከተማ እንዴትስ የአፍሪካ መዲና፣ እንዴትስ ሜትሮፖሊታን ልትባል ትችላለች?👇
👉በአገሪቱ ግማሽ ሕዝብ ላይ የተፈጸመው ወንጀል የበለጠ የሚያሳፍረን በአዲስአበባ ካሉት መስጊዶች 70% በአምልኮቦታ አፈቃቀድ መመሪያ ቁ1 የወጣውን«አንድ የአምልኮ ቦታ በትንሹ ከ2000-4000 ካሜ መሆን አለበት» የሚል መሥፈርት እንደማያሟሉ ስንረዳ ነው!👇
👉አንዲት "መቶ ዓመት አልፎኛል፤ ሜትሮፖሊታን ነኝ" ብላ ለምታምን ከተማ በዚህ ደረጃ ሙስሊም ነዋሪዎቿን መናቋ እጅግ ያሳፍራል! ይህንን ነውር መቀየር የከተማው መሥተዳድር፣ የሕዝበ ሙስሊሙ፣ የኦርቶዶክሱ፣ የፕሮቴስታንቱም ሆነ የሌላው ግዴታ ነው።👇
👉መሥተዳድሩ ይህንን ያደፈ ነውሩን እንዲያስተካክል በጉዳዩ ዙሪያ ንቃትና መነቃቃት መፍጠር፣ በተግባራዊ ንቅናቄ የታጀቡ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎችን ማካሄድ እና በጉዳዩ ላይ ያለውን ዝምታ ማናጠብ ይገባል።👇
👉ቢሮክራሲው ውስጥ ተሠግሥገው ከተማዋ በሠለጠነ የሜትሮፖሊታን ሕግ እንዳትመራ የሚያደርጉ፣ የግል ሃይማኖተኝነታቸውን የሌላውን ሃይማኖት ተከታይ መብት በመሸራረፍ የሚገልጹና ኋላ ቀር አመለካከት የሰነበተባቸው ጽንፈኞችንም ማጋለጥ ይገባል!👇
👉በተለይ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ሕዝበ-ሙስሊም በየአካባቢው ያለውን ተጨባጭ በማሳየትም ጭምር በተመሳሳይ ሐሽታግ በጉዳዩ ዙሪያ መጻፍ፣ መነጋገር፣ አጀንዳ ማድረግ አለበት። ለምሳሌ #መስጊድየምትጠላዋከተማ የሚል ሐሽታግ ልንጠቀም እንችላለን።👇
👉ይህ የከተማዋ አስቀያሚ ነውር በእኛ ትውልድ ማክተም አለበት። ትግል ካለ ምንጊዜም ድል ይኖራል። #እኩልነት እና #አካታችነት የአንድ የሠለጠነ ከተማ መሠረት ነውና ይህንን መሰል ትግል ማድረግ የሚያኮራ ነው።👇
👉ከዚያም ባለፈ ደግሞ ይህን መሰል ለፍትህ በሚደረግ ትግል በፍትህ እና እኩልነት የሚያምን ኦርቶዶክስ፣ ፕሮቴስታንትም ሆነ ሌላው አዲስ አበቤ (አቴይስቱንም ጨምሮ) ከጎናችን እንደሚቆም እርግጠኛ መሆን እንችላለን! ምን ትላላችሁ?👇
የዛውያ ጥናታዊ ፊልም 👇
.

• • •

Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh
 

Keep Current with Isaac Eshetu

Isaac Eshetu Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

PDF

Twitter may remove this content at anytime! Save it as PDF for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video
  1. Follow @ThreadReaderApp to mention us!

  2. From a Twitter thread mention us with a keyword "unroll"
@threadreaderapp unroll

Practice here first or read more on our help page!

More from @isuchisu

21 Aug 20
ኦሮሚያ ላይ ግርግር ሲፈጠር የሌላ ብሄር አባላት ላይ አሰቃቂ ጥቃት የሚፈጽሙት፣ የዓይን ምሥክሮች እና የአካባቢው ሰዎች «ከአሁን በፊት አይተናቸው የማናውቃቸው ናቸው» የሚሏቸው ሰዎች በመንግሥት ወታደሮች ሲነኩ አናይም። 1/
👉 ዘግናኝ ግድያዎችን ፈጽመው፣ የንጹሃንን ሕይወት ቀጥፈው፣ የፈለጉትን ንብረት አውድመው ይሰወራሉ። ፖሊሶች ቪዲዮ ይቀርጿቸዋል። ጥይት የሚተኩስባቸው የለም። ሁሉም «ትእዛዝ አልተሰጠንም» ብለው ንፁሃን ሲጠቁ በዝምታ ያልፋሉ። 2/
👉 በሌላ በኩል ተቃውሟቸውን እና ቁጣቸውን ለመግለጽ ወደጎዳና የሚወጡ ኦሮሞ ወጣቶች ሴት ወንድ፣ ወጣት ጎልማሳ ሳይባል በጥይት አናታቸው ይነደላል። ደማቸው ያለስስት ይፈስሳል። ቤታቸው ድረስ ተኪዶ ይገደላሉ። የሚወጡት ፎቶዎች እጅግ ያሰቅቃሉ። 3/
Read 5 tweets
26 Jul 20
Thread: ነውረኛ መነጽራችሁን አውልቁ!

1/ ሁሉንም ፀብ እና ችግር በሃይማኖት ማዕቀፍ መመልከት ለማናችንም አይጠቅምም። ለሚዲያ ማጥላያ ዘመቻ ይጠቅም ይሆናል። ለአገር ግን አይጠቅምም። 👇
2/ መንገድ ላይ አንድ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ሰው ሠርቆ ሲሮጥ ብታየው «አንድ ኦርቶዶክስ ሠርቆ ሲሮጥ አየሁ» ብለህ መናገር እጅግ ነውር ነው። ሃይማኖቱን ዒላማ ማድረግ ነው። ፍጽም ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ያፈነገጠ ነውር ነው። 👇
3/ መንገድ ላይ አንድ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ ሰው ሠርቆ ሲሮጥ ብታየው «አንድ ፕሮቴስታንት ሠርቆ ሲሮጥ አየሁ» ብለህ መናገር እጅግ ነውር ነው። ሃይማኖቱን ዒላማ ማድረግ ነው። ፍጽም ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት የማይጠበቅ ነውር ነው። 👇
Read 16 tweets
20 Apr 20
Thread below
እኒህን ሰዎች ስማቸውን ወደፊት እንፈልገዋለን፤ ባይሆን በባህሪ አይደንቲፋይ ማድረግ ይከብድ አይመስለኝም...
.
👉 በቀድሞው ሥርዓት ውዳሴ የተጠመዱ፤
.
👉 ለቀደሙ በደሎች ዛሬ ላይ አጋር የሚሆኑ፤
.
👉 እኩልነትን በተግባር የሚቀናቀኑ፤ 👇
👉 የመላውን ዜጋ አገር የአንድ ሃይማኖት የአንድ ባህል ርስት አድርገው የሚመለከቱ፤
.
👉 ኢትዮጵያ ከእነሱ ውጭ ባለ ሃይማኖት እና ባህልም ጭምር ስትገለጽ የሚኮሰኩሳቸው፤
.
👉 ሌላውን እንደመጤ ራሳቸውን እንደኦሪጅናል የሚቆጥሩ፤ 👇
Read 7 tweets
18 Apr 20
@ethiotelecom በክርስትያኑም በሙስሊሙም ቀረጥ የሚተዳደር ድርጅት ቢሆንም ለክርስትናና ለእስልምና በዓላት የሚለቃቸው የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክቶች ፍጹም የተለያዩ ናቸው። በቀጣዮቹ ትዊቶች ምስል እንደምታዩት ... 👇
👉የሙስሊም በዓላት ሲሆኑ በጥቅሉ በዓሉ የሠላም የፍቅር እንዲሆን በመመኘት ያልፈዋል። ተደራሹንም «የእስልምና እምነት ተከታዮች» በሚል ራሱን በማይጠቀልል መልኩ ያስቀምጣል። «እኛ» የሚል ነገር አያስገባም። 👇
👉የክርስትና በዓል ሲሆን ደግሞ መልዕክቱን መንፈሳዊ ቃና ያላብሰዋል። እምነቱን የሚጋራ እና የሚሳተፍበት መሆኑን በሚጠቁም መልኩ «እኛ» የሚል ቃና ይጨምርበታል። («የሕይወት ተስፋችን እንዲለመልም» እንደሚለው) ይህ ግልጽ መድልዎ ነው!👇
Read 6 tweets
7 Apr 20
እስከሚገባኝ ሱባዔ ለተወሰኑ ቀናት ተገልሎ የሚፈጸም ኦርቶዶክሳዊ ፆምና ጸሎት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ደሞ ኦርቶዶክስ ብቻ ሳይሆን ሙስሊምም፣ ፕሮቴስታንትም፣ ዋቄፈናም፣ ኢአማኝም ሌላም ነው። ለምን ኦርቶዶክሳዊ አምልኮ እንዲፈጽም ይጠየቃል?! 😓👇
👉 ሁሉም የየራሱ የአምልኮና የጸሎት ሥርዓት አለው። ሁሉም በሚያምንበት ጸሎት እንዲያደርግ መጠየቅ ጥሩ ነው። «ሕዝቡ ከጠ/ሚ ጀምሮ የ3 ቀን ሱባዔ ይግባ» ብሎ መጠየቅ ግን «የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ተጠምቆ ተዋህዶን ይቀበል» ከማለት ተለይቶ አይታይም!👇
👉 ጊዜው የመከራ ነው። ፈተና መጥቶብናል። ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ኦርቶዶክሱም፣ ሙስሊሙም፣ ጴንጤውም ተባብሮ ለሕዝብ ደኅንነት ማልቀስና በትብብር መረባረብ አለበት። ያ ማለት ግን በአምልኮዎቻችን መካከል ያሉ ድንበሮች ይፈርሳሉ ማለት አይደለም!👇
Read 5 tweets
9 Mar 20
ትዳር የብሄር ገደብ የማይደረግለት መልካም ውህደት ነው። የተለያዩ ዜጎችም ሆነ ብሄሮች እርስ በእርስ እየተጋቡ መዋለዳቸው የሰውነታችን ማረጋገጫ፣ የሰዋዊ ትስስራችን መገለጫ ነው። ይህን ትስስር ለመበጠስ የሚሞክርን ማውገዝና መገሰጽ ተገቢ ነው።👇
👉 ከዚህ አንጻር ትናንት በOMN የቀጥታ ሥርጭት ላይ የብሄርን አጥር ዘልለው ያገቡ ጥንዶች እንዲፋቱ የቀሰቀሰችው ግለሰብ እጅግ ፀያፍ ንግግር መናገሯ የሚያወዛግብ አይደለም።👇
👉 አገራችን ላይ ከዱሮም ጀምሮ አንዱ ብሄር ከአንዱ ጋር እንዳይጋባ የመከልከል መጥፎ ልማድ ነበር። ከሌላ ብሄር የትዳር አጋር ማጨት የፈለጉ ወጣቶች የመጀመሪያ ጭንቀት «ቤተሰቤ እሺ አይለኝም» የሚለው ነበር።👇
Read 11 tweets

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just two indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3/month or $30/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!

Follow Us on Twitter!