My Authors
Read all threads
ትዳር የብሄር ገደብ የማይደረግለት መልካም ውህደት ነው። የተለያዩ ዜጎችም ሆነ ብሄሮች እርስ በእርስ እየተጋቡ መዋለዳቸው የሰውነታችን ማረጋገጫ፣ የሰዋዊ ትስስራችን መገለጫ ነው። ይህን ትስስር ለመበጠስ የሚሞክርን ማውገዝና መገሰጽ ተገቢ ነው።👇
👉 ከዚህ አንጻር ትናንት በOMN የቀጥታ ሥርጭት ላይ የብሄርን አጥር ዘልለው ያገቡ ጥንዶች እንዲፋቱ የቀሰቀሰችው ግለሰብ እጅግ ፀያፍ ንግግር መናገሯ የሚያወዛግብ አይደለም።👇
👉 አገራችን ላይ ከዱሮም ጀምሮ አንዱ ብሄር ከአንዱ ጋር እንዳይጋባ የመከልከል መጥፎ ልማድ ነበር። ከሌላ ብሄር የትዳር አጋር ማጨት የፈለጉ ወጣቶች የመጀመሪያ ጭንቀት «ቤተሰቤ እሺ አይለኝም» የሚለው ነበር።👇
👉 ይህ ብዙውን ጊዜ ከመናናቅ፣ አንዳንዴ ደግሞ «ባህላችን ስለማይመሳሰል አብሮ መኖር ያስቸግራል» ከሚል ሽፍንፍን አስተሳሰብ የፈለቀ ችግር ነበር። ብዙ ላጤዎችን haunt ያደረገ፣ አሁንም ሆንት እያደረገ ያለ ችግር ነው። የሚያውቅ ያውቀዋል።👇
👉 በተለይ ደግሞ የብሄር ትርክት በተጧጧዘባቸው ባለፉት ጥቂት ዓመታት እንደአዲስ ሳያገረሽብን አልቀረም። የተለያዩ ብሄር ሰዎች እንዳይጋቡ መጣር በራሱ ነውር ሆኖ ሳለ «የተጋቡትም ይፋቱ» የሚል ሐሳብ ማንፀባረቅ ደግሞ የእጥፍ እጥፍ ነውር ነው።👇
👉 ከዚህ አንጻር OMN የላይቭ ሥርጭት ላይ የተላለፈ የግለሰብ ሐሳብ መሆኑን ጠቅሶ ለማቋረጥ ሞክረው እንዳልተሳካላቸው መግለጹ፣ እንዲሁም ይቅርታ ጠይቆ ቪዲዮውን መሠረዙ መልካምና ተገቢ እርምጃ ነው። 👇
👉 ፖለቲከኞች መሪዎች ናቸው። መሪ ደግሞ ተመሪውን የመምራት ኃላፊነት አለበት። ግለሰቦች ከድንበር ያለፈ ንግግር ሲናገሩ፣ ጽንፈኝነት ሲታይባቸው መሪ ፖለቲከኞች ግለሰቦቹን መገሰጽ ግዴታቸው ነው። 👇
👉 ልጂቷ ያንን ንግግር ስታደርግ «እንዲህ አይባልም፤ ተሳስተሻል» ብሎ የሚመልሳት ፖለቲከኛ ሁሌም ሊኖር ይገባል። በወቅቱ ስብሰባው ላይ ይህ ተደርጎ ከሆነ መልካም ነው። ካልተደረገ ግን ለመሪዎቹ ትልቅ ጉድለት ነው።👇
👉 የትኛውም ፖለቲከኛ ከሥራዎቹ አንዱ የአካሄድ ችግሮችን ማረም፣ ተመሪውን መንገድ ማሳየትና መገሰጽ መሆኑን ሊገነዘብ ይገባል።

እርግጥ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተመሪን መገሰጽ አልተለመደም አውቃለሁ። ግን ልንለምደው የሚገባ ነገር ነው።👇
👉 ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአገሪቱ ሁሉም አቅጣጫዎች ፖለቲከኞች ሲያሳዩ የቆዩትን ባህሪ ማየት ተስፋ አይሰጥም። ፖለቲካችን ተበላሽቶ አክራሪነት ተስፋፍቷል። የራሱንም ተከታይ ቢሆን ሲያጠፋ የሚገስጽ ለእሴት ተገዥ የሆነ ፖለቲከኛ ያሻናል!👇
Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh.

Enjoying this thread?

Keep Current with Isaac Eshetu

Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

Twitter may remove this content at anytime, convert it as a PDF, save and print for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video

1) Follow Thread Reader App on Twitter so you can easily mention us!

2) Go to a Twitter thread (series of Tweets by the same owner) and mention us with a keyword "unroll" @threadreaderapp unroll

You can practice here first or read more on our help page!

Follow Us on Twitter!

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just three indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3.00/month or $30.00/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!