, 27 tweets, 3 min read
My Authors
Read all threads
Thread

የሁለት ስብሰባዎች ትዝታዬ

በቅርቡ ዲሲ በነበረኝ ቆይታ የጃዋርን እና የእስክንድር ህዝባዊ ስብሰባዎች የሚዲያ ሽፋን ለመስጠት የመገኘት እድሉ ገጥሞኝ ነበር። የመጀመሪያው ስብሰባ የጃዋር ነበር - ቅዳሜ እለት። 1/27
ከስብሰባው በፊት ቃለ ምልልስ ማድረግ ስለነበረብኝ እንዲሁም የአድራሻ ለውጥ ሲደረግ ስለዋለ፣ እኔና ባልደረባዬ በስፍራው የደረስነው ትንሽ ዘግየት ብለን ነበር። በር ላይ ግርግር ስለነበር፤ አዘጋጆቹ በጓሮ በር እንድንገባ ነግረውን ገባን። 2/27
ውስጥ ስንደርስ ዝግጅቱ ተጀምሮ ነበር። ሰው ጥቅጥቅ ብሏል፤ ከታች እስከ ፎቅ ድረስ ሞልቶ፣ ሰዎች ጥግጥጉን ይዘው ቆመዋል፤ አንዳንዶችም መሬት ላይ ቁጭ ብለዋል። 3/27
ባልደረባዬ እና እኔም ካሜራችንን አዘጋጅተን ከጨረስን በኋላ፣ ከኋላ ያሉትን ሰዎች ላለመከለል መሬት ላይ ቁጢጥ አልን። ባልደረባዬ ኦሮሚኛ ስለማይሰማ፣ ባይተዋርነት እንዳይሰማው አለፍ አለፍ እያልኩ መተርጎም ጀመርኩ። 4/27
ጃዋር መናገር ሲጀምር አዳራሹ ውስጥ ሰዉ ላይ የተለያየ ስሜት ይነበብ ነበር - እልህ፣ ምሬት፣ ቁጣ እንዲሁም በተወሰነ ደረጃ ኩራት። ጃዋር ንግግሩን ቀጥሏል፤ ሰዎች በመሀል በመሀል የተለያዩ ድምፆችን ያሰማሉ፤ 5/27
ከዛ ውጭ በሚገርም ጥሞና ይከታተሉ ነበር - በጩኸትና ጭብጨባ ዝምታው እስኪሰበር ድረስ። ቤቱ በኦሮሞ የትግል/የኦነግ ባንዲራ አሸብርቋል። የኢትዮጵያ ባንዲራ ለምልክትም ቢሆን አላየሁም፤ እውነት ለመናገር እኔም ጠብቄ አልነበረም። 6/27
ጃዋርን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ንግግር ካደረጉ በኋላ የገቢ ማሰባሰቢያ ሲጀመር፣ ከአስተናባሪዎቹ አንዱ መጣና "ኢትዮትዩብ ናችሁ" ብሎ ጠየቀኝ፤ አዎ አልኩት፤ "fundraising ልንጀምር ስለሆነ ካሜራችሁን አጥፉ፤ የOMN ካሜራም ጠፍቷል" አለን። 7/27
ትዛዙን ተቀብለን፣ ከሜራችንን አጥፍተን፣ እቃችንን ሰብስበን መውጣት ስንጀምር፣ ከታዳሚዎቹ አንዱ ጠጋ ብሎ ኢትዮትዩብ መሆናችንን ጠየቀን፤ አዎ ስንለው፣ "አሪፍ ስራ ነው የምትሰሩት" ብሎን፣ አመስግንነን ሳንጨርስ፣ 8/27
"ወደ እኛ ብትመጡ ጥሩ ነው" አለን። "እኛ" ውስጥ አነማን አንደተጠቃለሉ እሱ እና ፈጣሪ ብቻ ናቸው የሚያቁት። ውጪ ስንወጣ በዝናብ እና ጨለማ ውስጥ፣ በመንገድ ዳርና ዳር ሆነው የሚሰዳደቡ ሰዎች አጋጠሙን፤ የጃዋር ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች ነበሩ፤ 9/27
አንዳንዱ የሚያዝናና፣አንዳንዱ የሚያሳዝን ንግግር ነበር።ስለሀገሬ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት እየተሰማኝ ወደ መኪናችን አመራን።በማግስቱ እስክንድር የጠራው ስብሰባ ነበር።በስፍራው የደረስነው ስብሰባው ከተጠራበት ሰአት ትንሽ ቀደም ብለን ነበር።10/27
ለወትሮው በሰአት የመጀመር ችግር ያለበት እንዲህ አይነት ስብሰባ፣ ጭራስ ብዙ ሰው በጊዜ ደርሷል። አዳራሹ ውስጥ ስንገባ ሁለት ጉዳዮች አስገረሙኝ፦ አንደኛ ለስብሰባው የተዘጋጀው የአዳራሽ ስፋት፤ 11/27
ሁለተኛ ገና ሳይጀመር አዳራሹን መሙላት የጀመረው ህዝብ ብዛት። ኢትዮጵያን የሚያንቆለጳጵሱ ሙዚቃዎች በዲጄ አዳራሹ ውስጥ ይደመጣል፤ ከጥግ እስከ ጥግ አዳራሹ በኮከብ አልባው የኢትዮጵያ ባንዲራ አሸብርቋል፤ 12/27
ብዙም ሳልቆይ አዳራሹ ውስጥ ዮኒ ማኛ መገኘቱ ከመድረክ አካባቢ ተነገረ፤ ብዙዎችም በጭብጨባ እንኳን ደህና መጣህ አሉት። ዞር ዞር እያልኩ ፎቶ ማንሳት ጀመርኩ። ሌሎች የፖለቲካ ስብሰባዎች ላይ የማላገኛቸውን ብዙ ሰዎች አገኘው። 13/27
ጥቂት ቆይቶ ታማኝ በየነ ወደ አዳራሹ ገባ፤ ሞቅ ባለ አቀባበል ተቀበለው ታዳሚው። ቀጥሎም ታዳሚው በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው እስክንድር በሚገርም አጀብ ታጅቦ ወደ አዳራሹ ሲገባ ቤቱ በአንድ እግሩ ነበር የቆመው። 14/27
ተደጋግሞ ስለ አዲስ አበባ ይነገራል፣ የዘፈናል፤ ነገር ግን እንደ ከተማው ልጅነቴ አዳራሹ ውስጥ የነበረውን ስሜት መጋራት አልቻልኩም፤ ትናንት የተሰማኝ የሚጎረብጥ ስሜት ዛሬም ይሰማኛል፤ 15/27
አዳራሹ ውስጥ በታዳሚው ዘንድ የምመለከተው የእልህ፣ የሀዘን፣ የንዴት፣ የቁጭት ስሜት እዚህም አለ። ሁለቱ ስብሰባዎች የተገኘነው ተመሳሳይ ሰዎች ምናልባትም እኔ እና ባልደረባዬ ብቻ ሳንሆን አንቀርም። 16/27
ሆኖም ግን ተመሳሳይ ድብልቅልቅ ያሉ ስሜቶችን ከታዳሚው ላይ ተገንዝቤያለሁ - ስሜቶቹ የሚመነጩት በተለያየ፣ ምናልባትም በተቃራኒ ምክንያት ቢሆንም። ትናንት ለጃዋር ነብሱን ለመስጠት ዝግጁ የሚመስል ታዳሚ አየሁ፤ 17/27
ዛሬ ደግሞ ጃዋር ቢሞት ጮቤ ሊረግጥ የሚችል ታዳሚ አየሁ። ሁለቱን ስብሰባዎች አለማነፃጸር ከበደኝ። ሁለቱም ስብሰባዎች ላይ የነበሩት የገዛ ወገኖቼ ናቸው። ሁለቱም ጋር በግል የማውቃቸውን ወዳጆች አግንቼ ነበር። 18/27
ነገር ግን ለእኔ ወዳጅ የሆኑ፣ ነገር ግን ሁልቱ ስብሰባዎች ላይ የነበሩ እነዚህ ወገኖቼ ቢገናኙ የእግዜር ሰላምታ መለዋወጣቸውን አርግጠኛ አይደለሁም። እንዴት እዚህ ላይ እንደደረስን አላውቅም። 19/27
የትናንቱም፣ የዛሬውም ስብሰባዎች ውስጥ ራሴን ማግኘት አለመቻሌ ብቻ ሳይሆን፣ የአንድ ሀገር ልጆች ይሄን ያህል መራራቃቸውም ልቤን ሰብሮት፣ የበአድነት ስሜትም ውስጤን ወሮት ነበር - ሁለቱም ስብሰባዎች ውስጥ። 20/27
ወደ እስክንድር ስብሰባ ልመለስና፤ እስክንድር ለመናገር ሲነሳ ቤቱን ጩኸት ሞልቶት ነበር፤ ነገር ግን ንግግሩ ዘለግ እያለ ሲሄድ፣ የእስክንድር ድምጽ ረጋ ያለ መሆኑና ታዳሚውም በሚገርም ጥሞና ያዳምጥ ስለነበር፣ 21/27
በተደጋጋሚ የሚገርም ፀጥታ ቤቱን ይምላው ነበር። ዮኒ ማኛ አስተያየት ለመስጠት ሲነሳ የነበረው ጩኸት፣ በስብሰባው ማገባደጃ አካባቢ ምን ያህል ሰው ከቦት ሰልፊ ይነሳ እንደነበር ስመለከት፣ ህዝቤ ሆይ ማስተዋልህ ወዴት ነው? 22/27
የሚል ጥያቄ ፈጥሮብኝ ነበር። የእሁዱ ስብሰባ ተጠናቆ ወደ መኪናዬ ሳመራ፣ የመኪናዬ መስታወት ላይ የአብን በራሪ ወረቀት ተሰክቶ ጠበቀኝ። አዳራሹ ውስጥ ከነበረው ስሜት አንፃር፣ ይህንን flyer ማግኘቴ ብዙም አልገረመኝም። 23/27
ከወዳጆቼ ጋር እራት ለመብላት መንገድ ስንጀምር፣ በተከታታይ ቀናት በሁለቱ ስብሰባዎች የተሰማኝ የባይተዋርነት ስሜት አለቀቀኝም ነበር። የሁለት ሀገር ሰዎች ተጣልተው፣ እኔ የሶስተኛ ሀገር ሰው ሆኜ ሁለቱን እየጎበኘሁ ያለሁ ሁሉ መስሎኛል። 24/27
በጣም አሳሰበኝ። ከዚህ መካረር እንዴት ነው የምንወጣው? እስክንድር እና ጃዋር መነጋገር ቢችሉ ኖሮ ሁለቱ ስብሰባዎች እንዲህ የተካረረ ስሜት ይኖራቸው ነበር? በማህበረሰባችን ውስጥ ልሂቃን ሲራራቁ ተከታዩም መራራቁ የማይቀር ነው። 25/27
ብዙ ጊዜ የምንከተለው ሰዎችን ስለሆነ፤ እሴቶችን ስላልሆነ ማለት ነው፤ ዐቢይን፣ ብርሀኑን፣ ጃዋርን፣ እስክንድርን ስለሆነ የምንከተለው። የማይነጋገሩ መሪዎችን ስንከተል፣ እርስ በእርስ መነጋገር እናቆማለን። 26/27
የሚያዋጣን ሁላችንም ወደ መሀል መምጣት ብቻ ነው። ዳር እና ዳር ቆመን ገመዱን ስንጎትት፣ መበጠሱ አይቀርም። ማዶ ለማዶ መቆም ሁላችንንንም ባዶ እንዳያስቀረን እሰጋለሁ።27/27
Missing some Tweet in this thread? You can try to force a refresh.

Enjoying this thread?

Keep Current with Alemayehu Gemeda

Profile picture

Stay in touch and get notified when new unrolls are available from this author!

Read all threads

This Thread may be Removed Anytime!

Twitter may remove this content at anytime, convert it as a PDF, save and print for later use!

Try unrolling a thread yourself!

how to unroll video

1) Follow Thread Reader App on Twitter so you can easily mention us!

2) Go to a Twitter thread (series of Tweets by the same owner) and mention us with a keyword "unroll" @threadreaderapp unroll

You can practice here first or read more on our help page!

Follow Us on Twitter!

Did Thread Reader help you today?

Support us! We are indie developers!


This site is made by just three indie developers on a laptop doing marketing, support and development! Read more about the story.

Become a Premium Member ($3.00/month or $30.00/year) and get exclusive features!

Become Premium

Too expensive? Make a small donation by buying us coffee ($5) or help with server cost ($10)

Donate via Paypal Become our Patreon

Thank you for your support!